የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በስኬት እንዲጠ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በስኬት እንዲጠናቀቅ በርካታ ስራዎች እየተከናወኑ ነው፡- የአዲስ አበባ ሰላም እና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ

የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በስኬት እንዲጠናቀቅ በርካታ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ሰላም እና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ።

ቢሮው ጉባኤው በስኬት እንዲጠናቀቅ የሚያስችል የውይይት መድረክ ከባለድርሻ አካላት ጋር እያካሄደ ይገኛል።

በውይይት መድረኩ የ ቢሮ ኃላፊዋ ሊዲያ ግርማ የአፍሪካ መሪዎች ጉባኤ በስኬት እንዲጠናቀቅ ቢሮው በርካታ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ገልጸዋል።

ባለፉት ጊዜያት ከተማዋ የተለያዩ ሀይማኖታዊ እና ባህላዊ በአላትን በስኬት ማጠናቀቋን የጠቆሙት ኃላፊዋ በርካታ አለም አቀፍ እና አህጉር አቀፍ ኮንፈረንሶችን በድምቀት ማከናወኗንም ገልጸዋል።

የከተማችን ነዋሪዎች በተለመደው ኢትዮጵያዊ ጨዋነት እንግዶችን እንዲቀበል ጥሪ ያስተላለፉት ቢሮ ኃላፊዋ የአፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ከተማችን ታላላቅ አህጉርአቀፍ እና አለምአቀፍ ጉባኤዎችን በብቃት የማስተናገድ አቅሟን አሁንም ይበልጥ የምታጎላበት እንደሚሆንም ጨምረው ጠቅሰዋል::


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.