ከንቲባ አዳነች አቤቤ ሀብተጊዮርጊስ ድልድይ በተ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ሀብተጊዮርጊስ ድልድይ በተለምዶ ኬሻ በጠረባ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በእሳት አደጋ የደረሰውን ጉዳት ጎብኝተዋል::

የእሳት አደጋው ሌሊት የተከሰተ መሆኑን የገለጹት የአዲስ አበባ እሳት እና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ኮማንደር አህመድ መሃመድ በአካባቢ ያሉ ቤቶች የተገነቡበት ግብአት፣ የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታዉ እንዲሁም አካባቢው የአደጋ ጊዜ ተሽከርካሪዎችን አለማስገባቱ ተደማምሮ የእሳት አደጋዉ እንዲሰፋ ምክንያት መሆኑን ተናግረዋል።

ኮማንደር አህመድ መሃመድ ጨምረው አደጋውን ለመቆጣጠር የእሳት አደጋ ሰራተኞች በፍጥነት ደርሰው ሰፊ ርብርብ ያደረጉ መሆኑን ጠቅሰው አካባቢው መኪና የማያስገባ በመሆኑ እና ሌሎች ተቀጣጣይ ነገሮች በመኖራቸው ምክንያት የተለያየ መጠን ያለው ጉዳት መድረሱንም ጨምረው ገልጸዋል::


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.