ከሁሉ በማስቀደም የረዳን እና ያከናወነልን ፈጣሪ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ከሁሉ በማስቀደም የረዳን እና ያከናወነልን ፈጣሪ ይመስገን!ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ዛሬ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት ያስመረቅነው የአዲስ አለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማእከል ለከተማችን ብሎም ለሀገራችን አዳዲስ እድሎችን የሚከፍት፣ የማያቋርጥ የሃብት ምንጭ መፍጠሪያ የሚሆን እንዲሁም ለገጽታ ግንባታ እና ለቱርስት ስበት ትልቅ ሚና የሚጫወት ማዕከል ነው::

ማዕከሉ አለምአቀፋዊ ኮንፍራንሶችን፣ የንግድ ውይይቶችንና ስምምነቶችን፣ ባህላዊ መድረኮችንና ልዩ ልዩ ኤግዚቢሽኖችን ለማስተናገድ እንዲሁም አዳዲስ ሃሳቦች የሚንሸራሸሩበት የንግድና የኢኮኖሚ ስምምነቶች የሚጎለብቱበት ነው::

15ሺ ካሬ የውጪ ሁነት ማስተናገጃ ቦታ ያለው የአዲስ አለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማእከል ባለ 5 ኮከብ ዘመናዊ ሆቴል፣ ሪስቶራንቶች፣ የስፖርት፣ የጤና፣ የመዝናኛ እና የልዩ ልዩ አገልግሎት መስጫን  ያከተተ ግዙፍ ማዕከል ነዉ።

ከዚህም ባሻገር፣ በአንድ ጊዜ እስከ 2000 ተሽከርካሪዎችን ማቆም የሚችል ፓርኪንግ ያለዉ ሲሆን የለሚ ፓርክ እና በቀጥታ ከአየር መንገድ  ጋር የሚያገናኝ ሰፊ የመንገድ መሰረተ ልማትም ከማዕከሉ ጋር ተያይዞ በመጠናቀቅ  ላይ ይገኛል ፤ይህም ኢኮኖሚያችንን የሚያነቃቃ፣ ሰፊ የስራ እድል የሚፈጥር ከመሆኑ በላይ እንግዶች ሲመጡ ያለምንም እንግልት ሁሉንም አገልግሎቶች በአንድ ስፍራ እንዲያገኝ ተደርጎ የተሰራ ነው፡፡

ይህ ስራ ከዳር እንዲደርስ የቅርብ ድጋፍና ክትትል ላደረጉልን ለክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ዶ/ር ዐብይ አሕመድ ከፍ ያለ ምስጋናና አክብሮቴን በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም ላቀርብ እወዳለሁ::

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.