
የንግዱ ማህበረሰብ የተፈጠረለትን እድል ለመጠቀም የሚያስችለዉ ጊዜ ላይ ደርሷል።ከንግድ እና ዘርፍ ማህበራት የተወከሉ ተሳታፊ ጎብኚዎች
የንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከልን ጎበኙ
በዛሬዉ እለት የንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከልን ጎብኝተዋል።
ጉብኝቱም የሀገራችንን የንግዱን ማህበረሰብ በንግድ ስርዓት ዉስጥ በማስተሳሰር ከተቀረዉ ዓለም ጋር ተወዳዳሪነትን መፍጠር የሚያስችል ጉዞ ላይ ሀገሪቱ መሆኗን ለማመላከት ነው ተብሏል።
ማዕከሉም ዘርፈ ብዙ አገልግሎትን በመስጠት በኩል ለሀገራችን የመጀመሪያዉ መሆኑና ተወዳዳሪነቱ ከሀገር አልፎ ከዉጩ ክፍለ ዓለም የራሷን ማንነትና ሀገር በቀል ምርቶች እንዲሁም ቅርሶቿን በማስተዋወና የቱሪዝም ኮንፈረንስን በማሳደግ ረገድ ጉልህ ድርሻ ያለዉ መሆኑና በዚህም ሀገራችን ወደ ከፍታ የማንሰራራቷን ዘመን ማሳያ መሆኑን አስጎብኚዉ አካል ገልጿል።
ጎብኚዎችም በበኩላቸዉ ማዕከሉ የንግዱን ማህበረሰብ ብቻ ሳይሆን ለቀጣይ ትዉልድም ታሳቢ ያደረገ ስራ መሠራቱን ገልፀዉ ይህም የሀገራችን የቀደምትነት ታሪኳን በድጋሚ አግዝፎ ያሳየ ነዉ ብለዋል ።
ለነጋዴዉ ማህበረሰብ ምርቱን ከማስተዋወቅና ከመሸጥ ባሻገር ከተቀረዉ ዓለም ጋር አቅሙን አሳድጎ ለመወዳዳር ልዩ ዕድል ተፈጥሮለታል ሲሉ በመደመም አስተያየታቸዉን ሰጥተዋል።
በቴክኖሎጂ ሽግግር በኢንቨስትመንት በቱሪዝም ኮንፈረንስ በትስስር ኢኮኖሚዉን ከማሳደግ ባሻገር ማህበረዊ ግንኙነቶችን በማጠናከር እየተሠራ ባለዉ ስራ የንግዱ ማህበረሰብ የተፈጠረለትን እድል ለመጠቀም የሚያስችለዉ ጊዜ ላይ መድረሱ አመላካች ነዉ ብለዋል።
ይህ የሚያሳየን መንግስት በሁሉም ዘርፍ ፀጋዎቿን መጠቀም መጀመሯንና በኢኮኖሚና በማህበራዊ ዘርፉ የሚጠቅም አስደማሚ ስራዎችን እየሠራች መሆኗን ያረጋገጥንበት በመሆኑ በማንኛዉም በኩል የድርሻችንን ለመወጣት ዝግጁ ነን ሲሉ ጎብኚዎቹ አረጋግጠዋል ።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.