አፍረካን ሊደርሺፕ ሜጋዚን ከንቲባ አዳነች አቤቤን የአፍሪካ ምርጥ ሴት መሪ በሚል ሸለመ፤
አፍረካን ሊደርሺፕ ሜጋዚን የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤን የአፍሪካ ምርጥ ሴት መሪ በሚል ሽልማት አበረከተላቸዉ።
መቀመጫዉን በእንግሊዝ ያደረገዉ እና በየአመቱ በአፍሪካ ምርጥ ብቃት ያሳዩ አፍሪካዉያን መሪዎችን የሚሸልመዉ የአፍሪካን ሊደርሺፕ ኦርጋናይዜሽን የፈረንጆቹን 2024 የሽልማት ስነስርቱን በአዲስ አበባ አከናዉኗል።
በስካይ ላይት ሆቴል የተከናወነዉ የሽልማት ስነስርአት በኢትዮጵያ የአመቱ ምርጥ ሰዉ በሚል ሲካሄድ የመጀመሪያዉ ነዉ።
የአፍረካን ሊደርሺፕ ኦርጋናይዜሽን አካል የሆነዉ አፍሪካን ሊደርሺፕ መጋዚን የአመቱን ምርጥ ሰዉና መሪ በላቀ የአመራር ብቃት የሚሸልም ሲሆን የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤም ሽልማቱን የአፍሪካ ምርጥ ሴት አመራር በሚል ተሸልመዋል።
ሽልማቱን የተቀበሉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ሽልማቱ ስለተበረከተላቸዉ አመስግነዋል።
“የማይበገር የአፍረካን ኢኮኖሚ መገንባት” በሚል መሪቃል የተካሄደዉ የሽልማት ስነስርአቱ ከ25 በላይ የሚሆኑ እና በተለያዩ ደረጃዎች የሚገኙ አፍረካዉያን መሪዎች የተገኙበት ነዉ።
የማይበገር ኢኮኖሚን መገንባት ችለዋል የተባሉት እና በአመራራቸዉ ዘላቂ የሆነ ኢኮኖሚያዊ እድገትን ለማስመዘገብ የላቀ ሚና ያላቸዉ አመራሮች የተሸለሙበትም ስነስርአት ነዉ።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.