የአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል ከተመረቀ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል ከተመረቀ በኋላ ጉብኝቱ እንደቀጠለ ነዉ

በዛሬዉ ዕለት የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት እና  ሲቪክ ማህበራት  እንዲሁም የሴትና ወጣት ክንፍ ማዕከሉን ጎብኝተዋል።

ከተማችን አዲስ አበባ የምታካሒደዉ ሁለተናዊ የልማት ስራዎች ለሀገራችን ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ ብሎም ለሌሎች ዓለም ሀገራት  ተምሳሌትነቷን ያረጋገጠጠችበት መሆኑን የገለፁት ጎብኚዎቹ ይህ ጅምር እንጂ ያበቃ ስራ ባለመሆኑ ኢትዮጵያን የሚመጥኑ ስራዎች ተጠናክረዉ መቀጠል አለባቸዉ ሲሉ ተናግረዋል።

እንደ ፖርቲ በሚያለያዩን ላይ ዉይይትና መቻቻልን እያስቀደምን አንድ በሚያደርጉን ላይ በጋራ እየተሳሰርን መንግስት ከሚሠራቸዉ አካታች የልማትና መሠል ተግባራት ላይ በትብብር መስራታችንን ይበልጥ የሚያጠናክርልን ሆኖ አግኝተነዋል ብለዋል ።

ያደጉ ሀገራት ቀዳሚ አድርገዉ  የሠሩት ትዉልድ ግንባታ ላይ በመሆኑ ዘላቂ ዉጤት አስመዝግበዋል  መንግስትም  ያለንን አቅም ለይቶ ሀገርና ትዉልድን መሠረት ያደረጉ ዘመን ተሻጋሪ ስራዎች ላይ በቁርጠኝነት በመስራቱ  ወደ ቀዳሚነታችን የሚያስፈነጥሩን የልማት ትሩፋቶች በአጭር ጊዜ  ለማየት ችለናል ሲሉ በጉብኝታቸዉ ወቅት ሀሳባቸዉን አጋርተዋል።

ይህንንም ከትዉልድ ትዉልድ  ማሰቀጠል ለመንግስት ብቻ የሚተዉ ሳይሆን በሀገሪቱ ያሉ ፖርቲዎች እና  ሲቪክ ማህበራት ሌሎችም ኃላፊነትና  ግዴታ ጭምር በመሆኑ ወጣቱ ትዉልድ በሚደረጉ የልማት ስራዎች የበኩሉን በመወጣት የራሱን ታሪክ እንዲፅፍ በጋራ እንሰራለንም ሲሉ አረጋግጠዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.