የአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል በተለያዩ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል በተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እየተጎበኘ ይገኛል

በአዲስ አበባ ከተማ  የሚገኙ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች  የአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከልን በዛሬዉ እለት ጎብኝተዋል።

በጉብኝታቸዉ ወቅት እንደገለፁት መንግስት የሀገሪቱን ዜጎች ወደ ብልፅግና ማማ የሚያሻግር በርካታ  ስራዎችን እየሠራ መቆየቱን ገልፀዉ ይህም ዛሬ የጎበኘነዉ ግዙፍ ማዕከል የሀገራችንን እድገት ያስመሠከረ ሌላዉ ስኬት ነዉ  ብለዋል ።

አክለዉም ኢትዮጽያ ያሏትን ፀጋዎች ለማስተዋወቅና ለመሸጥ እንዲሁም ኢኮኖሚዋን ይበልጥ ለማሳደግ ማዕከሉ የማይተካ ሚና እንዳለዉ  ግንዛቤ የጨበጥንበት ይህንንም በከተማችን ማየታችን የምንኮራበት ልዩ  ድምቀት ነዉ ሲሉ በአድናቆት ገልፀዋል።

ትዉልዱን መሠረት ያደረጉ ተወዳዳሪነታችንን የሚያጎሉ የልማት ስራዎች ላይ ከመንግስት ጎን ተሠልፈን የምንሠራበት ወቅት ላይ እንገኛለን ያሉት ጓብኚዎቹ በቀጣይም ሌሎች አስደማሚ ስራዎችን በመስራት የሀገራችንን ገዕታ ይበልጥ የምናጎላበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም  ሲሉ አስተያየታቸዉን ሠጥተዋል።

በመጨረሻም መንግስት እያደረገ ላለዉ ስራ አድናቆትና ምስጋናቸዉን ገልፀዉ  በእነዚህ የልማት ስራዎች ሳንኩራራ ሁላችንም በአንድነት ተባብረን  ተጨማሪ ድሎችን ማስመዝገብ  የዚህ ትዉልድ ኃላፊነት ነዉ በማለት መልዕክታቸዉን አስተላልፈዋል።

ይህ ግዙፍና ዘርፈ ብዙ  የአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል ለተከታታይ አስር ቀናት ለጎብኚዎች ክፍት ነዉም  ተብሏል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.