አዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል ገቢን ከማ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

አዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል ገቢን ከማሳደግ ባሻገር የመንግስትን የውጪ ምንዛሬ ለማዳን ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ማዕከሉን የጎበኙ የከተማዋ ነዋሪዎች ገለፁ።

ማዕከሉ ለጉብኝዎች በይፋ ክፍት በሆነ በ 3 ቀናት ውስጥ በተለያዩ የሙያ ዘርፍ የተሰማሩ አካላት እና የከተማዋ ነዋሪዎች በመጎብኘት ላይ ናቸው።

በጉብኝቱ ወቅት የጉብኝቱ ተሳታፊዎች እንደገለጹት የአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል ሙሉ በሙሉ አግልግሎት መስጠት ሲጀምር ከአለም ዳርቻ የሚመጡ አምራቾች እና አቅራቢዎች የሚገናኙበት ዋና መደረሻ እንደሚሆን ገልፅዋል፡፡

የሀገሪቱን የኮንፈረንስ ቱሪዝም ከማሳደግ ባሻገር የመንግስትን የውጪ ምንዛሬ ፍላጎት ማሳደግ የሚያስችል ነው ሲሉም ተናግረዋል።

ሀገራችን ከተቀረዉ አለም ሃገራት ጋር የንግድ ስርዓቱን በማስተሳሰር የኢኮኖሚዉ ዘርፍ እንዲያድግ ከሰራቻቸዉ በርካታ ተግባራት አንዱ እና ዋነኛዉ የአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል ማሳያ መሆኑን እና በተሰራው ስራም የዜግነት ኩራት ተሰምቶናል ብለዋል ።

ለሀገር ዉስጥ ወጣቶች የስራ እድል ለመፍጠር እና ለንግዱን ማህበረሰብ በሀገር ዉስጥ ንግድ ብቻ ሳይገደብ ከዓለም የንግድ ስርዓት ጋር ተቀላቅሉ ለመወዳደር ትልቅ ዕድል ይፈጥራል ሲሉም የከተማዋ ነዋሪዎች ተናግረዋል ።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.