
ከሀይማኖት ተቋማት የተወከሉ አባቶች ፣ አባ ገዳዎች፣ ሀደ ሲንቄዎችና የሀገር ሽማግሌዎች አዲስ አለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከልን ጎበኙ።
ከአራት ቀን በፊት የካቲት 22 ቀን 2017 ዓ.ም ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት የተደረገው አዲስ አለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል ለተከታታይ 10 ቀናት የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እየተጎበኘ ይገኛል።
በዛሬው እለት ደግሞ ከሀይማኖት ተቋማት የተወከሉ አባቶች ፣ አባ ገዳዎች፣ ሀደ ሲንቄዎችና የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም የተለያዮ የህብረተሰብ ክፍሎች ማዕከሉን ጎብኝተዋል።
የጎብኙት ተሳታፊዎች እንደተናገሩት ፦በአይነቱአዲስ እና የመጀመሪያ የሆነ የቴክኖሎጂዎችን አሟልቶ የያዘ አዲስ አለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል የግብርና እና የማዕድን ምርቶችን እንዲሁም የተለያዩ ምርቶችን በአንድ ማዕከል ማስተዋወቅ በሚያስችል መልኩ መገንባቱ በቀጣይ ለሚሰራቸው ስራዎች ልምድ የሚወሰድበት ነው ብለዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.