መንግስት ለሀገርና ለትዉልድ የሚበጁ ስራዎችን...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

መንግስት ለሀገርና ለትዉልድ የሚበጁ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን በተጨባጭ ማየት ችለናል። የኢፌድሪ መከላከያ ጤና ዋና መምሪያ



በዛሬዉ ዕለት የኢፌድሪ መከላከያ ጤና ዋና መምሪያ አመራርና አባላት  የአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከልን ጎብኝተዋል።

ከጉብኝቱ ጎን ለጎን መምሪያዉ ለመከላከያ ሰራዊት አባላት ከመስመራዊ መኮንን እስከ  ከፍተኛ መኮንን የማዕረግ ማልበስ ስነ-ስርዓት በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል አካሒዷል።

የኢፌድሪ መከላከያ ጤና ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጀነራል ጥጋቡ ይልማ  ጉብኝቱንና የማዕረግ ማልበስ ስነ.ስርዓቱን አያይዘዉ እንደገለፁት 129ኛዉን የአድዋ ድል በዓልን ባከበርንበት ማግስት ላይ ሁነን እንዲሁም የሀገራችን ትልቅ ሀብት የሆኑትን  ህዝብና ፀጋዎቿን በመጠቀም ዲጂታል ኢትዮጽያን ለመገንባት በሚያስችላት የአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል ተገኝተን የታሪክ ተጋሪ መሆናችን መርሀ ግብሩን ልዩ ያደርገዋል ብለዋል።

አክለዉም ሀገራችን በሪፎርም ለዉጥ መሆኗንና በርካታ አመርቂ ዉጤቶችን እያስመዘገበች መገኘቷን  ጠቅሠዉ ይህም ማሠብ ብቻ ሳይሆን መተግበር  እንደምትችል ያሳየችበት ሌለኛዉ እዉቀት የማስተሳሰር ብቃት የታየበት ግዙፍ ማዕከል መሆኑን ተናግረዋል።

በአካል የጠነከረ በአዕምሮ የዳበረ ብቃት ያለዉ አስተማማኝ የሀገር አለኝታ ሠራዊት ለመፍጠር ማዕከሉ የማይተካ ሚና እንዳለዉ ገልፀዉ የኢፌድሪ መከላከያ ጤና ዋና መምሪያም የጀመረዉን የሪፎርም ስራ በማጠናከር የዘመነ አገልግሎት ለመሥጠት  ሀገራችን በቴክኖሎጂ የደረሰችበትን ጉዞ ማፋጠን እና ሰላምን በዘላቂነት ማስጠበቅ ከሁሉም ዜጋ ይጠበቃል ሲሉ አስተያየታቸዉን ሠጥተዋል።

ለማዕረግ ተሸላሚዎችም ይህ ታሪካዊ ሁኔታ በተሠማራችሁበት የስራ ኃላፊነት ቃልን በተግባር የምትፈፅሙበት ሀገር ከእናንተ ተጨባጭ ዉጤት  የምትጠብቅበት መሆኑን አዉቃችሁ የራሳችሁን ታሪክ እንድትሰሩ ያሉት  የመምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጀነራል ጥጋቡ ይልማ  አያይዘዉም  የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክታቸዉን አስተላልፈዋል።

የኢፌድሪ መከላከያ ጤና ዋና መምሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ ሌተናል ኮ/ል እያዩ ምህረቱ በበኩላቸዉ ሠራዊቱ ለሠላም በሚከፍለዉ ዋጋ መንግስት  ለሀገርና ለትዉልድ የሚበጁ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን እና ተጨባጭ  ውጤቶት እተመዘገቡ መምጣታቸውን በጉብኝታችን ለማየት ችለናል ብለዋል።

አክለዉም ሀገራችን በሀገረ መንግስት ግንባታ ቀዳሚ እንደነበረችና በቀዳሚነቷ በአፍሪካም ሆነ ከሌሎች አለም ሀገራት በሁለተናዊ መስኩ ኃላፊነቷን በመወጣት ህያዉ ታሪክ ያላት መሆኑን ጠቅሠዉ በዚህ ትዉልድም እንደሀገር  ሊመጥኑ የሚችሉ አደምንታ ያላቸዉ ስራዎች እየተሰሩ ናቸዉ ብለዋል።

በመጨረሻም ትዉልዱ ሀገራችን በኢኮኖሚ በማህበራዊ  እያደረገች ያለዉን ዘለቂ  የእድገት ጉዞ  ዉስጥ ልክ አንደ ጀግኖቹ አባቶችና እናቶች የራሱን ታሪክ በመስራት የታሪክ አሻራዉን የማኖር ኃላፊነት አለበት ሲሉ መልዕክታቸዉን አስተላልፈዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.