ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ የታክስ ዕዳ ያ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ የታክስ ዕዳ ያለባቸው 62 ግብር ከፋዮች ከሀገር እንዳይወጡ የእግድ ትዕዛዝ ማስተላለፉን የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ገለፀ፡፡

በዛሬው እለት የኪነ ጥበብ ዘርፍ ባለሙያዎችን ጨምሮ ተማሪዎችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከልን ጎብኝተዋል።

በጉብኝታቸዉም እንደገለፁት ማዕከሉ ካደጉት ሀገራት ጋር በማንኛውም የስራ መስክ ብቁ ሆኖ ለመወዳደር መሠረት የጣለ መሆኑን ገልፀዉ በዚህ ትዉልድ ባለ ብዙ ዘርፍ ሀገራዊ ቅርስ ማየታችን ለቀጣዩ ትዉልድ የበለጠ እንድንሰራ ያነሳሳል ብለዋል።

ማዕከሉ ብዙ ዘርፎችን በአንድ አቅፎ መያዙ ለሁለተናዊ ፈጣን እድገት ያለው አበርክቶ ከፍተኛ በመሆኑ ሁላችንም በተሰማራንበት የስራ መስክ ልንጠቀምበት ይገባል ሲሉም የጉብኝቱ ተሳታፊዎች ገልፀዋል ።

የተሰራው ስራ በተለይም በኪነ ጥበብ ዘርፋ የነበሩ ክፍተቶችን የሚሞላ የቱሪዝም ዘርፋን በማሳደግ ለሃገር እድገት የበለጠ አስተዋፅኦ የሚያበረክት ፕሮጀክቶች እንደሚሆን ተናግረዋል።

በመጨረሻም አሁን ላይ በከተማችን እየተሰሩ የሚገኙ የተለያዪ ፕሮጀክቶች ሃገርና ትውልድን አንድ አድርገው የሚያስቀጥሉ መሆናቸውን የኪነ ጥበብ ባለሙያዎ በሰጡት አስተያየት አስረድተዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.