ቢሮው "የዕምነት ተቋማት በሰላም ግንባታና በልማ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ቢሮው "የዕምነት ተቋማት በሰላም ግንባታና በልማት ሂደት ውስጥ ያላቸው ሚና" በሚል ርዕሰ ጉዳይ የዕምነት ተቋማት ኃላፊዎች እና የአስተዳደር ሰራተኞች ጋር በከተማ ደረጃ የማጠቃለያ የሰላም ኮንፈረንስ አካሄደ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ቢሮ በሁሉም ክ/ከተሞችና ወረዳዎች የዕምነት ተቋማት በሰላም ግንባታና በልማት ሂደት ውስጥ ያላቸው ሚና" በሚል ርዕሰ ጉዳይ  ሲካሄድ የቆየው ኮንፈረንስ ዛሬ በከተማ ደረጃ ማጠቃለያ መርሃ ግብር አካሂዷል።

መድረኩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ ሊድያ ግርማ የለውጡ መንግስታችን በኢትዮጵያ ያሉ የሃይማኖት ተቋማት በሀገራቸው የለውጥ ጉዞ እኩል የመሳተፍ በር በመክፈት በሀገሪቱ ውስጥ ያሉ ሁሉም እምነቶች እኩል እውቅና እንዲኖራቸው፤አስተምሮአቸውንም ለተከታዮቻቸው በነፃነት እንዲያስተምሩ ለሁሉም እኩል እድል በመሰጠቱ ምክንያት በእምነት ተቋማት ለረጅም አመታት ተከፋፍሎ የነበሩ ሀይሎች መንግስት ዋጋ በመክፈል በጋራ አንድ አድርጎዋል። ኢትዮጵያ በምታከናውናቸው የልማት፣የሰላም፣የለውጥ ጉዞ ውስጥ እኩል ተሳታፊ እንዲሆኑ የለውጡ መንግስት አበክሮ ሰርቷል፡፡ እየሰራም ይገኛል ብለዋል።

የቢሮ ኃላፊዋ አክለውም የሃይማኖት ተቋማት እንደ አስተምህሯቸው ለሰው ልጅና ለአገር ሰላም መሆን  አበክረው እየሰሩ ይገኛሉ። ሚሊየኖች የሚሳተፉበት የተለያዩ አለማዊ አህጉራዊ  እና ከተማዊ መልክ ያላቸው ሃይማኖታዊና ባህላዊ እሴቶቻቸውን ጠብቀው በሰላም ተከብረው እንዲአልፉ ጉልህ ሚና ተጫውተዋል ብለዋል። ለዚህም ለሁሉም የሀይማኖት ተቋማት ምስጋና አቅርበዋል።

የቢሮ ሀላፊው አክለውም አሁን ባለንበት ወቅት የፓለቲካና የግልና የቡድን ፍላጎታቸውን የሀይማኖት ካባ በመልበስ ለማሳካት የሚሰሩ የጥፋት ሀይሎች የእምነት ተቋማት አበክረው እንዲከታተሉና እንዲያርሙ አሳስበዋል። በውስጥ የሚፈጠር ችግር የእምነቱ አስተምሮ በሚፈቅደው መልክ በውይይት እንዲፈቱ አስገንዝበዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ፀሃፊ መጋቢ  ታምራት አበጋዝ በበኩላቸው የሃይማኖት ተቋማት በውስጣቸው እና ከሌሎች ጋር የሚያደርጉት ምክክር የውስጥ ጥንካሬን የሚፈጥር ሲሆን ለእርስ በርስ መተማመን እና ለጋራ ራዕይ በጋራ መስራትን በማጎልበት በሃይማኖት መካከል መከባበርን፣ መተባበርን እና አብሮነትን በማሳደግ ጥርጣሬን እና ስጋትን የሚቀርፍ ነው ብለዋል።

የሃይማኖት ተቋማት አገረ መንግስት ግንባታ ውስጥ ትልቅ ሚና እንዳላቸው አንዱ ማሳያ የአደባባይ በአላት በሰላም እንዲከበሩ በአብሮነት እየተመካከርን ማክበራችን እና  የተለያዩ የልማት ስራዎች ማለትም ትምርህት ቤት፣ ሃኪም ቤት እና የመሳሰሉት በእምነት ተቋማት በመሰራት አግልግሎት እየሰጡ መሆኑ ነው። አሁንም አገርን የሚወድ ትውልድ ለመቅረፅ የሃይማኖት አባቶች አርያ መሆን ይገባል ብለዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.