በነዳጅ አቅርቦት እና ስርጭትን በሚደነግገው አዋ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በነዳጅ አቅርቦት እና ስርጭትን በሚደነግገው አዋጅ ላይ ውይይት ተካሄደ

የአዲስ አበበባ ንግድ ቢሮ፣ በህዝብ ተወካዮች ምክርት ቤት በጸደቀውና በቀጣይ ተግባራዊ በሚደረገው  የነዳጅ አቅርቦት እና ስርጭትን በሚደነግገው አዋጅ ላይ ከነዳጅ አቅራቢ ኩባንያዎች እና ከነዳጅ ማደያ ባለቤቶች  ስራ አስኪያጆች ጋር በአዋጁ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት አካሂዷል፡፡

በውይይቱ ላይም አዋጁ ህገወ ጥነትን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት ውጤታማ እንደሚያደርገው ተሳታፊዎቹ ገልጸው፣ ተግባራዊ ከመደረጉ በፊት በሁሉም ደረጃ አገልግሎቱ ላይ ለሚሳተፉ አካላት ተመሳሳይ የግንዛቤ መፍጠሪያ መድረኮች መካሄድ  እንደሚገባቸው አንስተዋል፡፡

የነዳጅ ማደያ ባለቤቶች በበኩላቸው፣ ከቢሮው ጋር በመተባበር ማህበራዊ ኃላፊነታቸውን በመወጣት ረገድ በርካታ ተግባራትን እያከናወኑ መሆናቸውን አንስተዋል፡፡

በዚህም ዓመት ቢሮው የአቅመ ደካሞችን ቤት ለማደስ የሚያስችል ዕቅድ ያቀረበ ሲሆን የማደያ ባለቤቶቹም በቀረበው ዕቅድ ደስተኛ መሆናቸውን እና የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን  ከአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.