አዲስ አለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከልን የአዲ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

አዲስ አለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከልን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አመራሮች ፣ መምህራን፣ተማሪዎች እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጎበኙ።

በአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ አመራሮች መምህራን ፣ተማሪዎች፣ የስፓርት ቤተሰብ፣ የሜጋ ፕሮጄክት አመራሮችና ሰራተኞች አዲስ አለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከልን ጎብኝተዋል።

የጉብኝት ተሳታፊዎች እንደተናገሩት አዲስ አበባ ከተማን የቱሪዝም ማዕከልነቷን የሚያጎሉ የተለያዩ አወደ ርዕይ ኤግዚቭሽኖችን በማስተናገድ በዓለም አቀፍ ደረጃ ጉልህ ድርሻ ያላት ለማድረግ የሚያግዝ ማዕከል እንደሆነም ተገልጿል።

አዲስ አለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል የእኔነት ስሜት የሚፈጥር በቀጣይ በሃገራችን የተሻለ ስራ ለመስራት የሚያነሳሳ ነውም ብለዋል።

ከተማችን በልማት ስራዎች የደረሰችበትን ደረጃ መገንዘብ የቻልንበትና እና ይበልጥ ለፈጠራ ስራ የሚያነሳሳ ስራ መሰራቱን በሰጡት አስተያየት ተናግረዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.