በሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ዘርፉ የመንግስት ዋና ዋ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ዘርፉ የመንግስት ዋና ዋና አጀንዳዎችን ከማስረጽ አንጻር ውጤታማ ስራዎች ተሰርተዋል-መንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

በበጀት አመቱ ግማሽ አመት እቅድ በሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ዘርፉ የመንግስት ዋና ዋና አጀንዳዎችን ከማስረጽ አንጻር ውጤታማ ስራዎች መሰራታቸውን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።

የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ የግማሽ ዓመት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ "ዓላማ ተኮር፤ የተናበበ እና የተቀናጀ የተግባቦት ስርዓት ለእመርታዊ እድገት" በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ከበደ ዴሲሳ፥ በግማሽ ዓመቱ ዘርፉ መንግስታዊ አጀንዳዎችን ከማስረጽ አንጻር ውጤታማ ስራዎች ሰርቷል።

ዘርፉ ህዝብን በልማት ከማሳተፍ እና ከማነቃቃት አንጻርም አበረታች ስራዎች መከናወኑን ገልጸዋል።

በተለይም የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር፣እንዲሁም የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በተሳካ መልኩ እንዲከናወን ዘርፉ በጎ አስተዋጽኦ ማበርከቱን አንስተዋል።

በተጨማሪም እንደ አገር በትኩረት እየተከናወነ በሚገኘው የኮሪደር ልማት ስራ በህዝብ ተሳትፎ እንዲታገዝ ዘርፉ ትልቅ ሚና መጫወቱን ተናግረዋል።

በተመሳሳይ እንደ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀን እና የሰንደቅ ዓላማ ቀን የመሳሰሉ አገራዊ ሁነቶች ከተገቢው መልዕክት ጋር መሸፈናቸውን ጠቅሰዋል።

እነዚህ ሁነቶችም ለሰላም ግንባታ እና ህብረ ብሄራዊ አንድነትን በመገንባት ሂደት ትልቅ ውጤት ነበራቸው ብለዋል።

በሌላ በኩል የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ዘርፉ ከዘላቂ ሰላም ግንባታ እንዲሁም አፍራሽ መረጃዎችን ከመከላከል አንጻር አሁንም ብዙ ስራዎች እንደሚቀሩ ማውሳታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በመድረኩ ላይ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታዎች፣ የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት ሀላፊዎች፣ የኮሙኒኬሽን ዘርፍ ሃላፊዎች እና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል።

#GCSEthiopia

ለተጨማሪ መረጃ

https://linktr.ee/addisababacommunication


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.