
የአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ እና የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማተባበሪያ ኮሚሽን አመራሮች እና ባለሙያዎች የአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬክሽን ማዕከልን ጎበኙ
በዛሬዉ እለትም የአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ እና የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማተባበሪያ ኮሚሽን አመራሮች እና ባለሙያዎች፣በጎ ፈቃድ አገልግሎት የሚሰጡ ወጣቶች እንዲሁም የተለያዩ የከተማዋ የህብረተሰብ ክፍሎች የአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬክሽን ማዕከልን ጎብኝተዋል።
የጉብኝት ተሳታፊዎች እንደገለፁት ከተማዋ ሀገር አቀፍ አህጉር አቀፍና ዓለም አቀፍ ሁነቶችን የምታስተናግድ ከመሆኗ ባሻገር ዓለም አቀፍ ተቋማት የሚገኙባት በመሆኑ ማዕከሉ ሲገነባ የተለያዩ ዘርፎችን ታሳቢ ያደረገና ከዘመኑ የቴክኖሎጂ እድገት ጋር ተጣጥሞ የሚሔድ መሆኑን ገልፀዉ ይህም ለከተማዋ እድገት ሚናው የጎላ ነው ብለዋል።
ይህም ሀገራችን በጤናዉ ዘርፍ እየተገበረች ያለዉን የሪፎርም ስራዎች ይበልጥ የሚያጠናክርና ዉጤታማ ለማድረግ የሚያግዝ መሆኑን ጠቁመዋል።
በመጨረሻም የከተማችን ነዋሪዎች እና የተለያዩ ተቋማት የሚሳተፉበት በኢኮኖሚዉ ዘርፍ ራሳቸዉን ጠቅመዉ ሀገራቸዉን የሚጠቅሙበት ከተቀረዉ አለም ጋርም የሚተዋወቁበት ዕድል የሚፈጥር ነዉም ብለዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.