
እንኳን ለዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን አደረሳችሁ፣ አደረሰን!
ዘንድሮ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን ስናከብር የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ከሚያስችሉ ስራዎች ምን ያህል አሳካን፣ ምን ያህል ሴቶችን ህይወት የቀየሩ ፕሮጀክቶችን አጠናቅቀን፣ ምን ያህል ሴቶችን ተጠቃሚ አደረግን እንዲሁም ምን ያህል ቅድሚያ ለሚገባቸው ሴቶች ቅድሚያ መስጠታችንን በተግባር አረጋገጥን በማለት እና ለሌሎች ተደማሪ ድሎች ራሳችንን በማዘጋጀት ነው።
ከዚህ አንፃር ለከተማችን ሴቶች ተጠቃሚነት የሰራናቸው ስራዎች ፍሬ አፍርተዋል ፤ ግን በቂ ስላልሆኑ የሴቶችን አቅም ይበልጥ እያጎለበትን፣ እስካሁን ያገኘናቸውን ስኬቶች አጠናክረን ለበለጠ ተጠቃሚነት በትጋት መስራታችንን እንቀጥል እላለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.