የፌዴራል መንግሥት የሱፐርቪዥን ቡድን በአዲስ አ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የፌዴራል መንግሥት የሱፐርቪዥን ቡድን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለአንድ ሳምንት የሚቆይ የሱፐርቪዥን ሥራ ጀመረ፤

በፌዴራል መንግስት ከፍተኛ አመራሮች የተዋቀረው የሱፐርቪዥን ቡድኑ በዛሬው እለት በከተማ አስተዳደሩ የተመረጡ ክፍለ ከተሞች ላይ የሱፐርቪዥን ስራ የጀመረ ሲሆን በቀጣይ ቀናትም በቀሪ ክፍለ ከተሞች ላይ የሚያካሂድ ይሆናል።

የሱፐርቪዥን ቡድኑ ዛሬ በተመለከታቸው ክፍለ ከተሞች በ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት በተለያዩ ዘርፎች የተከናወኑ ተግባራት ሪፖርት በክፍለ ከተሞቹ አማካኝነት ቀርቧል።

በቀረቡት ሪፖርቶችም በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ክፍለ ከተሞቹ የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን ያከናወኑ መሆኑን ለሱፐርቪዥን ቡድኖቹ ገለፃ አድርገዋል።

የሱፐርቪዥን ቡድኑ በቀጣይ ቀናቶች በተቀሩ ክፍለ ከተሞች ላይ የሱፐርቪዥን ስራውን የሚቀጥል ሲሆን በተለያዩ ወረዳዎች እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን በአካል ተገኝተው እንደሚጎበኙ ታውቋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.