የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በዛሬው 4...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በዛሬው 4ኛ ዓመት 8ኛ መደበኛ ስብሰባ በሚከተሉት አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል::

1. ሀገራዊ እና ማህበራዊ ፋይዳ ላላቸው የማኑፋክቸሪንግ እና ሌሎች ፕሮጀክቶች የሚውሉ የቦታ ጥያቄዎችን መርምሮ አፅድቋል::

2. መደበኛ ያልሆነ የጎዳና ላይ ንግድን ሥርዓት ለማስያዝ ይረዳ ዘንድ የተዘጋጀ ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቶ አፅድቋል::

3. በምሽት የንግድ ቤቶች እና የትራንስፖርት አገልግሎት መስጫ ለማራዘም በወጣው ደንብ ዝርዝር  ላይ ተወያይቶ አፅድቋል::

4. የተርሚናል አገልግሎት አሠራር እና ቁጥጥር ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቶ አፅድቋል::

5. የአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ አደረጃጀት እና አሠራርን ለመወሰን የተዘጋጀ ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቶ አፅድቋል::

6. የመብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለሥልጣን ማቋቋሚያ ደንብ ቁጥር 166/2016 ለማሻሻል የወጣ ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቶ አፅድቋል::

7. የገርቢ የመጠጥ ውሃ ግድብ ፕሮጀክት ለመተግበር የቀረበ የውሳኔ ሀሳብ ላይ ተወያይቶ በሙሉ ድምፅ ውሳኔ አሳልፏል::


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.