በዛሬው እለት የአዲስ አበባ ከተማ መምህራን ማህ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በዛሬው እለት የአዲስ አበባ ከተማ መምህራን ማህበርን ጨምሮ የተለያዩ ማህበረሰብ ክፍሎች የአዲስ አለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል ጉበኙ::

የጉብኝቱ ተሳታፊዎች እንደገለፁት ግዙፍ  እና ዘርፈ ብዙ የሆነዉ የአዲስ አለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል በዚህ ትዉልድ  ተገንብቶ  የሀገርን ገፅታ እና  እድገት በሚያመላክት መልኩ ተገንብቶ እንደዚህ በማየታችን ደስታ ተሰምቶናል ብለዋል::

አክለዉም መምህራን ትዉልድን በመልካም ስነ ምግባርና እውቀት በመቅረፅና በመገንባት ረገድ ያላቸዉ ኃላፊነት  የላቀ በመሆኑ ለዚህ ደግሞ የአዲስ አለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል በእዉቀት ሽግግር ላይ የማይተካ ሚና እንደሚኖረው ተናግረዋል።

የሀገርን ፀጋዎች በሀገር ዉስጥ እዉቀት በመጠቀም ከዓለም ሀገራት ጋር ተወዳዳሪ መሆን እንደሚቻል ብቻ ሳይሆን ተወዳዳሪ መሆን መቻላችንን የሳየንበት እንዲሁም ገናና ስምና ታሪካችንን በዚህ ዘመን አጉልተን ያወጣንበት በመሆኑ ኩራት ተሰምቶናል ሲሉ ጎብኚዎቹ አስተያየታቸዉን ሰጥተዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.