
ማምሻውን የአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል ግንባታ ከጅማሮው አንስቶ በስኬት እስኪጠናቀቅ ድረስ አስተዋጽኦ ያበረከቱ አካላትን አመስግነናል::
ስንተባበርና በአንድነት ስንሰራ ስራዎቻችን ጥራት ያለዉ እና ዉጤታማ ይሆናል። ተግዳሮቶችን በመሻገር የጎደለውን እየሞላን ሀገራችንን ከፍ የሚያደርጉ ትላልቅ ስራዎች ለመስራት አቅም እየፈጠርን ሁላችንም ለስኬት እንደምንበቃ አዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል ትልቅ ማሳያ ነው::
ማዕከሉ ዓለምአቀፍ ደረጃውን የጠበቀ እና ለሀገር ያለውን ጠቀሜታ በመገንዘብ ለስኬት እንዲበቃ አስተዋጽዖ ያበረከቱ የማዕከሉ የቦርድ እና የማኔጅመንት አባላት፣የስራ ተቋራጩ እና አማካሪ ድርጅቱ፣ ባለአክሲዮኖች፣ ለልማት ከአካባቢው የተነሱ ነዋሪዎችን እንዲሁም ስራውን ያስተባበሩ የከተማችን አመራሮች እና ሰራተኞችን በሙሉ በራሴና በከተማ አስተዳደራችን ስም ላመሰግናቸው እወዳለሁ::
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.