
የወንዞች ዳርቻ ልማትና ብክለትን ለመከላከል በወጣው ደንብ ቁጥር 180/2017 ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት ተደረገ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደ የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ከአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር “ንፁህ ወንዝ ለጤናማ ህይወት!” በሚል መሪ ቃል የወንዞች ዳርቻ ልማትና ብክለትን ለመከላከል በወጣው ደንብ ቁጥር 180/2017 ላይ ከአምራች እና አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ጋር የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና አካሂደዋል።
በአዲስ አበባ ከተማ ገባር ወንዞችን ጨምሮ 76 ወንዞች መኖራቸውን የገለጹት የአዲስ አበባ ከተማ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዲዳ ድሪባ እነዚህ ወንዞች ለረጅም አመታት የቆሻሻ መጣያ እና የኢንዲስትሪ ፍሳሽ ማስወገጃ ቦይ ሁነው መቆየታቸውን አስታውሰዋል፡፡
አሁን ላይ በወንዞች ዳርቻ ልማት መርሃ ግብር እነዚህን ወንዞች በማልማት ለከተማችን ነዋሪዎች ምቹና ሳቢ ለማድረግ መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ብለዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በበኩላቸው ህዝባችን በማሳተፍ አዲስ አበባን እውነተኛ የአፍሪካ መዲና ከተማ ለማድረግ እና በወንዞች ዳርቻ የሚፈሱ ውሃዎችን ንፁህ በማድረግ ከብክለት ለመጠበቅ የወጣው ደንብ የሚያግዝ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
አክለውም በደንቡ አተገባበር ላይ ለወንዞች ብክለት መነሻ ይሆናሉ ተብለው ከሚታሰቡ ተቋማት ጋር የሚደረገው የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ተናግረዋል፡፡
የውይይት ተሳታፊዎችም የተሰጠው ስልጠና ስለወጣው ደንብ አፈፃፀሙን በተመለከተ በሚገባ እንዲረዱ እንዳደረጋቸው ተናግረው የተጀመረዉ የቅድመ ግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ ከቅጣት በፊት የበለጠ ማስፋት ማስተማርና ማሳወቅ እንደሚገባ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.