የፌዴራል የሱፐር ቪዥን ቡድን በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ የመስክ ምልከታ ማካሔድ ጀመረ።
በአቶ ሳዳት ነሻ በሚኒስትር ማእረግ የፌደራል ዲሞክራሲ ስርአት ግንባታ ማእከል አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ የተመራው የፌደራል ከፍተኛ የሱፐርቪዥን ቡድን በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ በ2016 ዓ.ም በትምህርት ለትውልድ ፣ በስራ እድል ፈጠራ፣ የከተማ ግብርና እና ሌማት ቱሩፋት ስራዎች፣ በህብረተሰብ ተሳትፎና በጎፍቃድ እንዲሁም በተለያየ ዘርፍ የተሰሩ ተግባራትን ከክፍለ ከተማ እሰከ ወረዳ አልፎም እሰከ ብሎክ ድረስ በመውረድ የተሰሩ ስራዎችን በዛሬው እለት በአካል የመስክ ምልከታ ማካሄድ ጀምረዋል።
በአሁኑ ሰዓት በክ/ከተማው በወረዳ11 አስተዳደር የተሰሩ የከተማ ግብርና እና የሌማት ቱሩፋት ስራዎች፣ የስራ እድል ፈጠራ ስራዎች፣ የትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ እንዲሁም ሌሎች የልማትና የመልካም አስተዳደር እንዲሁም አገልግሎት አሰጣጥ ስራዎችን ምልከታ በማካሔድ ላይ ይገኛሉ ።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.