.png)
የምስራቅ አፍሪካ የአገር ውስጥ ገቢ ሚኒስትሮችና ኮሚሽነሮች በመዲናዋ የተሰሩና እየተሰሩ የሚገኙ የልማት ስራዎችን ጎበኙ።
የምስራቅ አፍሪካ የአገር ውስጥ ገቢ ሚኒስትሮችና ኮሚሽነሮች ጉባኤ በአዲስ አበባ ከተማ መካሄዱ የሚታዎስ ሲሆን የጉባኤው ተሳታፊዎች በአዲስ አበባ ከተማ በግሉ ዘርፍ እና በሃገር ውስጥ ገቢ የተሰሩና እየተሰሩ የሚገኙ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል።
የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ አይናለም ንጉሴን ጨምሮ የምስራቅ አፍሪካ የአገር ውስጥ ገቢ ኮሚሽነሮችና ሚኒስትሮች ጉባኤ መካሄዱን ገልፀው የሚኒስትሮች ጉባኤ በኢትዮጵያ መካሄዱ በሃገር ውስጥ ገቢ ሰፋፊ የልማት ስራዎችን በራሳችን አቅም መስራት እንደምንችል ልምድ ያካፈልንበት ነው ብለዋል።
የምስራቅ አፍሪካ ሃገሪት የዓለም የገንዘብ ድርጅት ( IMF )ዋና ዳሬክተር ክላራ ማይራ በበኩላቸው በጉባኤው እና በጉብኝቱ ኢትዮጵያን ጨምሮ 7 የዓለም የገንዘብ ድርጅት ( IMF ) አባል ሃገራት መሳተፋቸውን አስረድተው በሃገር ውስጥ ገቢ በአዲስ አበባ ከተማ የተሰሩ የልማት ስራዎች ለሌሎች የምስራቅ አፍካ አገራት ልምድ የሚወሰድባቸው እንደሆኑ ተናግረዋል።
በጉብኝቱ የምስራቅ አፍሪካ የዓለም የገንዘብ ድርጅት ( IMF )ዋና ዳሬክተር ክላራ ማይራ ፣ የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ አይናለም ንጉሴን ጨምሮ 13 የምስራቅ አፍሪካ የገቢዎች ሚኒስትሮች እና ኮሚሽነሮች የአዲስ አለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል፣ የአድዋ ድል መታሰቢያ ፣ የወንዞች ዳርቻ የልማት ስራዎችን እና የኮሪደር ልማት ስራዎችን በመጎብኘት ተሳትፈዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.