"ኢትዮጵያ የአፍሪካ ኅብረት ልዩ የማኅበረሰብ ጤ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

"ኢትዮጵያ የአፍሪካ ኅብረት ልዩ የማኅበረሰብ ጤና ተቋም የሆነውን የአፍሪካ በሽታ መከላከል እና መቆጣጠር ማዕከል (Africa CDC) መቀመጫ በመሆኗ ክብር ይሰማታል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

በማዕከሉ ያሉት ላቦራቶሪዎች እና የምርምር አቅሞች በበሽታ መቆጣጠር ብሎም በወረርሽኞች እና ተላላፊ በሽታዎች ምላሽ በመስጠት ሥራ ከፍ ያለ ሚና ይጫወታሉ። ይኽ እድል ለሀገራችን የጤናው ዘርፍ ተመራማሪዎች እና ባለሞያዎች በአኅጉራዊ የምርምር ጥረቶች በመሳተፍ በዘመናዊ ላብራቶሪዎች እንዲጠቀሙም መንገድ ይከፍታል።

አባል ሀገራት ከአጋሮች ጋር በመተባበር ይኽን ተቋም ማጠናከር ይገባናል። በመሆኑም የአፍሪካ መሪዎች አኅጉራዊ የማኅበረሰብ ጤና ተቋማችን በመላው አኅጉራችን የጤና አገልግሎት በማሳደግ ላይ ተቀዳሚ በማድረግ ሥራ ላይ በሙሉ ኃላፊነት እንድንተባበር ጥሪ አቀርባለሁ።" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.