
ህብረ ብሄራዊ አንድነቷን የጠበቀች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የወጣቱ ተሳትፎ ሊያድግ ይገባል- አቶ ሞገስ ባልቻ
ህብረ ብሄራዊ አንድነቷን የጠበቀች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የወጣቱ ተሳትፎ ሊያድግ እንደሚገባ የብልጽግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ ገለጹ።
የአዲስ አበባ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ የወጣቶች ክንፍ ከተማ አቀፍ ውይይት ተካሂዷል።
̔ገዥ ትርክትን ለማስረፅ የመደመር ትውልድ ሚና ̕ በሚል በተካሄደው የወጣቶች የውይይት መድረክ ወጣቶች ህብረ ብሄራዊት ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ያላቸው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ፤ ወጣቶችን ያሳተፉ ስራዎች በተለያዩ እርከኖች ሲሰሩ መቆየታቸው ተነግሯል።
ብልፅግና ትውልድ ላይ ያተኮረ ፓርቲ መሆኑን ያነሱት የብልጽግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ ባለፉት ዓመታት የወጣቱን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሰፊ ስራ መሰራቱን ገልፀዋል። ባለፉት 6 ወራት በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ወጣቶች የስራ ዕድል መፈጠሩንም አንስተዋል።
ህብረ ብሄራዊት ሀገር ለመገንባት በሚደረገው ጉዞ ውስጥም ወጣቶች በንቃት መሳተፍ እንዳለባቸውም ተናግረዋል።
የብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የወጣቶች ክንፍ ፕሬዚዳንት መለሠ አባተ፤ ወጣቶች ገዥ ትርክቶች በማፅናት ሚናቸውን እንዲወጡ ሰፊ ስራዎች መከናወናቸውን አንስተዋል።
ወጣቶች የመደመር እሳቤ ላይ የተሻለ ግንዛቤ እንዲይዙ እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.