
ከአጎራባች ከተሞች ጋር በቅንጅት በተሰራ ስራ አስተማማኝ ሰላም ማስፈን ተችሏል- ወይዘሮ ሊዲያ ግርማ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና በኦሮሚያ ክልል የሸገር ከተማ አስተዳደር የሰላም እና ፀጥታ አስተዳደር የጋራ መድረክ እየተካሄደ ነዉ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላም እና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ ወይዘሮ ሊዲያ ግርማ፣ አዲስ አበባ ከነዋሪዎቿ ጋር በትብብር ከአጎራባች ከተሞችም ጋር በቅንጅት በሰራችዉ ስራ አስተማማኝ ሰላም የሰፈነባት እንድትሆን አስችሏታል ብለዋል፡፡
በቀጣይም ከአጎራባች ከተሞች ጋር በሰላም እና ፀጥታ ጉዳይ በቅንጅት ይሰራል ብለዋል፡፡
በመድረኩ ሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ባለፉት ጊዚያት ሰላም እና ፀጥታን ለማስፈን የተሰሩ የጋራ ሰራዎች ይገመገማሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በመድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ እና የሸገር ከተማ አስተዳደሮች ጉዳዩ የሚመለከታቸዉ አካላት ተገኝተዋል፡፡
AMN
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.