በአዲስ አበባ ከተማ ሲካሄድ በቆየው የሰራተኞችና...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በአዲስ አበባ ከተማ ሲካሄድ በቆየው የሰራተኞችና የአመራሮች ምዘና ውጤት ላመጡ ምደባ ተደረገ

በአዲስ አበባ ከተማ ሲካሄድ በቆየው የሰራተኞችና የአመራሮች ምዘና ውጤት ላመጡ ምደባ የተደረገላቸው መሆኑን የአዲስ አበባ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ አስታወቀ።

በተለዩ 16 ተቋማት የሪፎርም ስራ ሲያከናውን መቆየቱን ያስታወቀው የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ከሪፎርሙ ስራዎች አንዱ በሆነው የአመራሮችና ሰራተኞች ምዘና ከ19 ሺህ በላይ ፈተናውን የወሰዱ መሆኑን አስታውሷል። 

ከነዚህም ውስጥ አመራር 33.3 በመቶ እንዲሁም ሰራተኞች 50.6 በመቶ ያለፉ ናቸው ብሏል።

ፈተናውን ያለፉና ብቁ የሆኑ ሰራተኞችና አመራሮችም በየደረጃው ምደባ የተደረገላቸው መሆኑን አስታውቋል።

ቢሮው ከዝግጅት ምዕራፍ ወደተግባር ምዕራፍ መሸጋገሩንም ያስታወቀ ሲሆን በተለይም ሪፎርሙ ትኩረት ያደረገባቸው የቴክኖሎጂ ፣ የመዋቅራዊ አደረጃጀት ስራ፣ እንዲሁም የአሰራር ስርአት ማሻሻያዎችንና ብቃት ያለው የሰው ሀይል ግንባታ ተግባራዊ የማድረግ እንቅስቃሴ ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል። 

ለሁሉም ተፈታኞች የብቃት ስልጠና መስጠቱንም ያስታወቀው ቢሮው ተቋሙ ለደረሰበት የተግባር ምዕራፍ አመራሩ እገዛ ማድረግ እንዳለበትም ጥሪ አቅርቧል።

በቀጣይ ሪፎርም ውስጥ የሚገቡ ሌሎች ተቋማት መኖራቸውም ተጠቁሟል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.