
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምሁራንና የአስተዳደር ሰራተኞች በመዲናችን የተሰሩና እየተሰሩ ያሉ የልማት ስራዎች እየጎበኙ ይገኛሉ፡፡
ጉብኝቱም የአዲስ አለም ዓቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከልን፣ የገላን ጉራ የተቀናጀ ልማት መንደር፣ የቦሌ ክፍለ ከተማ ቡልቡላ ፓርክ ፣ የኮሪደር ልማት ስራዎችን እየጎበኙ ይገኛሉ።
የአዲስ አለም ዓቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል ተመርቆ ለአገልግሎት መብቃቱ አዲስ አበባ ከፍታዋን የሚያጎላ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ የተለያዩ ኮንቪንሽንና ኤግዚቢሽኖችን ለማስተናገድ አቅም ያለዉ ነውም ተብሏል።
የአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል እና በጉብኝታችን ያየናቸው በከተማ አስተዳደሩ የተሰሩ የልማት ስራዎች በአመራሩ በ 7/24 የስራ ባህል ተሰርቶ ዘርፈ ብዙ አገልግሎቶችን ለመስጠት በሚያስችል መልኩ ተገንብቶ ለዉጤት የበቃ መሆኑን ጎብኙዎች ተናግረዋል ።
ጎብኚዎችም በጉብኝታቸዉ ወቅት እንደተናገሩት የአፍሪካዊያን የአብሮነትና የአንድነት መገለጫ የኢትዮጵያዊያንም ኩራት መሆኑንና ተግባሩ መጠናከር እንዳለበት ተናግረዋል።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌን ጨምሮ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮችን ምሁራን እና የአስተዳደር ሰራተኞች የጉብኝቱ ተሳታፊ ናቸው ።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.