
#የጠሚሩምላሾች #PMOEthiopia
ኢኮኖሚን በተመለከተ
ባለፉት ስምንት ወራት በዋና ዋና የኢኮኖሚ አመላካቾች ታላላቅ ስኬቶች ተመዝግበዋል። በቀጣይ የበጀት ዓመቱ ቀሪ ወራት ይህን ስኬት ማጠናከር ከተቻለ ኢትዮጵያ በተያዘው በጀት ዓመት ከ8 ነጥብ 4 በመቶ በላይ የኢኮኖሚ እድገት ታስመዘግባለች።
ግብርናን በተመለከተ
"በግብርና ምርት የአነስተኛ አርሶ አደሮች የሰብል ሽፋን 20 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሄክታር ደርሷል። በስንዴ ልማትም በመኸር 4 ነጥብ 2 ሚሊዮን ሄክታር እንዲሁም በበጋ መስኖ ልማት 3 ነጥብ 7 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በስንዴ የተሸፈነ ሲሆን፤ በዚህም ከ300 ሚሊየን ኩንታል ያላነሰ ምርት ይስበሰባል ተብሎ ይጠበቃል። በቡና እና ሻይ ምርትም የተሻለ ስኬት እየተመዘገበ ነው። ለአብነትም ባለፉት ስምት ወራት ብቻ ከቡና ወጪ ንግድ 1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝቷል።"
ኢንዱስትሪን በተመለከተ
በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ስትሪንግ ኮሚቴ ተቋቁሞ በኢንዱስትሪ ዘርፉ ላይ ያሉ ማነቆዎችን የመፍታት ስራ ሲከናወን ቆይቷል። በዚህም የውጭ ምንዛሬ፣ የኃይል አቅርቦትና ሌሎች ችግሮች የተለዩ ሲሆን ችግሮቹን ለመቅረፍም እየተሰራ ነው። ለአብነትም በዘንድሮው ዓመት ብቻ ለኢንዱስትሪ ዘርፉ የቀረበው የኃይል አቅርቦት ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጻር የ50 በመቶ ብልጫ አለው። ከጥቂት ዓመት በፊት የአቅርቦት ጥያቄ የነበረበት የሲሚንቶ ምርትም አሁን ላይ ለውጭ ገበያ ጭምር ማቅረብ የሚያስችል አቅም እየተፈጠረ ነው። የኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅም 61 በመቶ የደረሰ ሲሆን፤ በዚህ ዓመት ብቻ 55 አዳዲስ ፋብሪካዎች ስራ ጀምረዋል።
አገልግሎት አሰጣጥን በተመለከተ
መንግስት የአገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል ሁለት ዋና ዋና ስራዎች መከናወን አለባቸው። አንደኛው በቀበሌ ደረጃ የተጀመሩ የለውጥ ስራዎች ሲሆን፤ እያንዳንዱ ቀበሌ አገልግሎት እንዲሰጥ ለማድረግ የሚያስችሉ አቅሞችን መገንባት ነው። በዚህም ሁሉም ቀበሌዎች ያላቸውን ሃብት በቁጥር ለይተው አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ነው። ይህ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። ሁለተኛው መሶብ የተሰኘ አገልግሎት ሲሆን በሙከራ ደረጃ በሲቪል ሰርቪስና በፕላንና ልማት ሚኒስትር በሲስተም ይጀመራል። አገልግሎቱም በአንድ መስኮት ሁሉንም አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ነው።
ገቢን በተመለከተ
ባለፉት ስምንት ወራት 580 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰብስቧል። ነገር ግን መንግስት የሚሰበስበው ገቢ ከጥቅል ሀገራዊ ምርት አንጻር ከ7 በመቶ አይበልጥም። ይህን ማሻሻል አለብን። በየአከባቢው የሚቀርቡ የልማት ጥያቄዎችን መመለስ የምንችለው ገቢያችንን በበቂ ሁኔታ ማሳደግ ስንችል ብቻ ነው።
የዋጋ ንረትን በተመለከተ
መንግስት በከፍተኛ ሁኔታ ድጎማ በማድረግ የዋጋ ንረቱ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ዜጎች እንዳይጎዳ በጥንቃቄ እየሰራ ነው። ለአብነትም መንግስት በአንድ ኩንታል ማዳበሪያ 3 ሺህ 700 ብር ይደጉማል። ለነዳጅም 72 ቢሊዮን ብር ተደጉሟል። በዚህም በሊትር 28 ብር እንደጉማለን። የደሞዝ ጭማሪ በማድርግም ቋሚ ገቢ ያላቸውን ዜጎች ገቢያቸው እንዲያድግ እየተሰራ ነው። ይህ ስራም ተጠናክሮ ይቀጥላል።
የአፈር ማዳበሪያን በተመለከተ
“እንደ ህዳሴ ግድብ ሁሉ የኢትዮጵያ ቀጣዩ ታላቅ ስራ የአፈር ማዳበሪያ ፋብሪካ ነው። ማዳበሪያ በሀገር ውስጥ ማምረት መጀመር አለብን ብለን ስራ ጀምረናል። ይህን ስራም በተለይ ከግሉ ዘርፍ ጋር በመተሳሰር ለመስራት እየተጋን ነው። አሁን ላይ ግን ኢትዮጵያ በየዓመቱ 24 ሚሊዮን ኩንታል ማዳበሪያ የሚያስፈልጋት ሲሆን፤ ይህን ፍላጎት ለሟሟላትም በየቀኑ 150 ሺህ ኩንታል ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ እያጓጓዝን ነው።”
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.