
የፕሪቶሪያ ስምምነትን በተመለከተ
“የፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረተ ልማቶችን በመመለስ የትግራይ ህዝብ አገልግሎት እንዲያገኝ አድርጓል። ያም ሆኖ አሁንም በበቂ ሁኔታ ያልተፈጸሙ ጉዳዮች አሉ። ከዚህም አንደኛው የታጣቂዎች ተሃድሶ (ዲዲአር) ስራ ነው። ይህ በዋናነት የሚጎዳው የትግራይ ህዝብን ነው። ወጣቶች በታጣቂ ስም ከመቀመጥ ወደ ልማት መሰማራት አለባቸው። በየወሩ ለልማት መዋል የነበረበት በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ለዚህ ስራ ይወጣል።
ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው በመመለስ ረገድም በራያና ጸለምት ጥሩ ስራ ተከናውኗል። በሌሎች አከባቢዎች ግን በተፈለገው ልክ አልሆነም። ይህ የሆነውም ሰብዓዊ ስራ እና ፖለቲካ የሚቀላቅሉ ኃይሎች በመኖራቸው ነው። ነገር ግን የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ባለፉት ሁለት ዓመታት ተጨማሪ ጦርነትን በማስቀረት ረገድ ከፍተኛ ስራ አከናውነዋል። ጊዜያዊ አስተዳደሩ የተሰጠው የሁለት ዓመት ጊዜ በማለቁ የህግ ማሻሻያ የሚፈልግ ጉዳይ አለ።ህግ ሲሻሻል ደግሞ የነበሩ አፈጻጸሞች መገምገም አለባቸው። በዚህም የፕሪቶሪያውን ስምምነት ባከበረ መልኩ መጠነኛ ለውጥ ከተካሄደ በኋላ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ስራውን እያከናወነ ህዝቡን ለምርጫ የሚያዘጋጅ ይሆናል። ይህን በተመለከተም ከጊዜያዊ አስተዳደሩ አመራሮችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይቶች እየተደረጉ ነው። በዚህ ሂደት ስራዎች ተገምግመው የግለሰቦች መቀያየር ሊኖር ይችላል።”
#የጠሚሩምላሾች
#PMOEthiopia
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.