
ሁለት የመርካቶ ቁጥር 1 መካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ተጠርጣሪ ሰራተኞችና ገንዘቡን ከንግዱ ማህበረሰብ ሲያሰባስቡ የነበሩ አምስት ተጠርጣሪ ነጋዴዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ገለፀ።
የግብር ተመን በአስተያየት እንገምትላችኋለን በማለት ከ1.7 ሚሊዮን ብር በላይ የተቀበሉ ሁለት የመርካቶ ቁጥር 1 መካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ተጠርጣሪ ሰራተኞችና ገንዘቡን ከንግዱ ማህበረሰብ ሲያሰባስቡ የነበሩ አምስት ተጠርጣሪ ነጋዴዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ገለፀ።
***
መጋቢት 2 ቀን 2017 ዓ/ም በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ልዩ ቦታው ሲዳሞ ተራ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ከሚገኙ አሮጌ ዕቃ እየገዙ ከሚሸጡ ነጋዴዎች ሁለት የመርካቶ ቁጥር 1 መካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሰራተኞች ነጋዴዎቹን በማነጋገር ለመንግስት የምትከፍሉትን የግብር የዋጋ ተመን አስተካክለን እንሰራላችኋለን ይሏቸዋል።
ይህንንም ለማስፈጸም እናንተ በአምስት ሰዎች አስተባባሪነት ከእያንዳንዱ ነጋዴ ብር አሰባስባችሁ የድርሻችንን ስጡን በማለት ከ89 ነጋዴዎች ከ1.7 ሚሊዮን ብር በላይ ሰብስበዋል።
የዚህን ድርጊት መፈጸም ከህብረተሰቡ መረጃ የደረሰው የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ሁለቱን የመርካቶ ቁጥር 1 መካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሰራተኞችና አምስቱን ነጋዴዎች መጋቢት 9 ቀን 2017 ዓ/ም ከነ ኤግዚቢቱ በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ እያጣራባቸው እንደሚገኝ ገልጿል።
ህጋዊነት የጎደለውን አካሄድ በመከተል ከመንግስት አሰራር ውጪ የንግዱን ማህበረሰብ በማሳሳት ባልተፈለገ አግባብ የግል ጥቅማቸውን የሚያስቀድሙና የተሰጣቸውን ኃላፊነት እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ሀገርን እና ህዝብን ለጉዳት የሚዳርጉ መሰል አካላት ሲገጥሙ የንግዱ ማህበረሰብም የጀመረውን ወንጀለኛን የማጋለጥ አበረታች ተግባሩን አጠናክሮ በመቀጠል ህጋዊ አሰራርን ሊከተል እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪውን ያቀርባል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.