እንኳን ለ1446 የታላቁ የረመዳን የፆም ወር አ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

እንኳን ለ1446 የታላቁ የረመዳን የፆም ወር አደረሳችሁ።

በመዲናችን ከሚገኙ አቅመ ደካሞችንም እና ዝቅተኛ ገቢ ካላቸዉ የእስልምና እምነት ተከታዮች ጋር የአፍጢር መርሃ ግብር አከናውነናል።

ይህን የጾም እና የጸሎት ወቅት የእምነቱ አስተምሮ በሚያዘው መሰረት ድሆችን እና ጠያቂ የሌላቸዉን ወገኖች መርዳት፣ መደገፍ እና አቅመ ደካሞችንም በማሰብ መሆን አለበት።
እኛም ፆሙን ምክንያት በማድረግ በከተማችን በሚገኙ 24ቱ የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከላት ዘወትር ማታ ማታ ለአቅመ ደካማ እና ለተለያዩ ማህበራዊ ችግሮች ለተጋለጡ ሰዎች የአፍጢር መርሃ ግብር በማዘጋጀት ነዋሪዎቻችንን እያስፈጠርን እንገኛለን::

በድጋሚ እንኳን ለ1446 የታላቁ የረመዳን የፆም ወር አደረሳችሁ::

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.