"24 ሰዓት የምትሰራ ፤.ለብልፅግና የምትተጋ ከ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

"24 ሰዓት የምትሰራ ፤.ለብልፅግና የምትተጋ ከተማ "በሚል መሪ ቃል ከተለያዩ የከተማዋ የንግድ ማህበረሰብ ጋር ከተማ አቀፍ ዉይይት ተካሔደ

በአዲስ አበባ ያለውን የንግድ እንቅስቃሴ ለማስፋት እና ህገወጥ ንግድን ለመቆጣጠር "24 ሰዓት የምትሰራ ፤.ለብልፅግና የምትተጋ ከተማ" በሚል መሪ ቃል  ከከተማዋ የንግዱ ማህበረሰብ ጋር ከተማ አቀፍ ዉይይት ተካሔዷል።

በውይይት መድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ እንደተናገሩት በከተማችን የዘመነ የንግድ ስርዓት ለማስፈን መንግስት ከነጋዴዉ ማህበረሰብ ከሸማቹና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በተሠራዉ የቅንጅት ስራ በኢኮኖሚዉ እና በማህበራዊዉ መስክ እንዲሁም በሌሎች አገልግሎት አሰጣጥ ዘርፈ ብዙ ስኬቶችን ማስመዝገብ መቻሉን ገልፀዋል፡፡

አቅርቦት መር የኢኮኖሚ ስርዓትን ስለምንከተል የምርት አቅርቦትን በሚያሳልጡ ዘርፎች ላይ ትኩረት ሰጥተን በመስራታችን ነጋዴዉ በሠብል ምርት በአትክልትና ፍራፍሬ እና በኢንዱስትሪ የምርት አቅርቦቶች ላይ ሚናዉን የተወጣበት መንግስትም  ገበያዉን ከማረጋጋት እና  ንግዱን ከማሳለጥ አኳያ ምቹ ሁኔታ የፈጠረበት ቅንጅታዊ ስራ መኖሩን አብራርተዋል፡፡

አክለዉም በከተማዋ የተሠሩ ሠፋፊ መሠረተ ልማቶች በምርት አቅርቦት እና ክምችት እንዲሁም በአቅራቢና በሸማቹ መካከል ግብይቱ ጤናማ በሆነ ፍትሀዊ የንግድ ስርዓት እንዲመራ አበርክቶዉ የጎላ መሆኑን ጠቅሠዉ  ከተማዋን የአፍሪካ የንግድ መዳረሻ ለማድረግ 24ሠዓት ሊሠራባት ማድረግ ይገባናል  ብለዋል።

የዛሬዉ ዉይይትም በትኩረት አቅጣጫ የተለዩ መሠረታዊ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርቶች አቅርቦት በማሳደግ ገበያ ማረጋጋት በሚቻልበትና በምሽት የንግድ እና የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሠጥ ለማድረግ የወጣዉን ደንብ ቁጥር 185 /2017 ከመተግበር አኳያ የጋራ ግንዛቤ ፈጥረን የጀመርነዉን ቅንጅታዊ አሰራር በማጠናከር በከተማችን የዘመነ የንግድ ስርዓት ለማስፈን እና የኢኮኖሚዉን ዘርፍ ለማሳደግ በጋራ ተግተን ልንሰራ ይገባል ሲሉ ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ መልእክታቸዉን አስተላልፈዋል::

የዘመነ የንግድ ስርዓት ለማስፈን እና ,ኢኮኖሚዉን ዘርፍ ለማሳደግ  የህግ ማዕቀፎች ጋር ተያይዞ  ከገቢ አሰባሰብ፤ከኮሪደር ልማት ተነሺ ነጋዴዎች፤ከብልሹ አሰራርእና ከአገልግሎት አሠጣጥ  እንዲሁም ከትራንስፖርትና ከፀጥታ አኳያ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ የተሰጠ ሲሆን በቀጣይ ቢታዩ እና ቢካተቱ ያሏቸዉ ላይ በሚመለከተዉ አካል ተገምግሞ በአሰራርና አተገባበር ማስፈፀሚያ ማንዋል ላይ ተካቶ ተግባራዊ እንደሚሆን ተመላክቷል፡፡

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ በበኩላቸው፣ በንግዱ ዘርፍ የተሰማሩ ነጋዴዎች መንግስት ባመቻቸላቸው የመስሪያ ቦታ እንዲሁም በተፈጠረላቸው የገበያ ትስስር የገበያ ማረጋጋት ስራ በአዲስ አበባ መሰራቱን ተናግረዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.