
ለወረዳ አመራሮቻችን ሲሰጥ የነበረውን ስልጠና ዛሬ አጠናቅቀናል።
ከተማችን ያለባትን ሃላፊነት ለመወጣት እና ለነዋሪዎቻችን ቀልጣፋ እና የላቀ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ብቁ እና የአገልጋይነት መንፈስ የተላበሰ አመራር በመገንባት ላይ እንገኛለን።
አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ የጀመርነው መሠረታዊ ለውጥና የሪፎርም ስራ ይበልጥ ውጤት እንዲያስገኝ እና ብቃት ያለው የህዝብ አገልጋይ ለመፍጠር የአመራሩ ሚና ትልቅ በመሆኑ ይህን አቅም ለማሳደግ የተሰጠ ስልጠና ነዉ።
በቀጣይም አገልግሎት አሰጣጥ ላይ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት የአመራር ምልመላና ስምሪት በብቃትና በክህሎት ላይ የተመሰረተ እንዲሆን በማድረግና ለነዋሪዎቻችን ጥራት ያለው እና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት ትኩረት ሰጥተን መስራታችንን እንቀጥላለን::
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/addisababacommunication
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.