
“የድጋፍ ስርዓታችንን እናሻሽል!” በሚል መሪ ቃል የዓለም የአእምሮ እድገት ውስንነት (Down syndrome) ቀንን ከዲቦራ ፋውንዴሽን ጋር አክብረናል።
ሃምሳ ሎሚ ለአንድ ሰው ሸክም ለሃምሳ ሰው ግን ጌጥ መሆኑን በመገንዘብ፣ የአእምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸው ህጻናትን በመደገፍ እና ለማህበረሰባችን በቂ ግንዛቤ በመፍጠር ረገድ ሁላችንም የበኩላችንን ኃላፊነት ልንወጣ ይገባል።
ዲቦራ ፋውንዴሽን በአእምሮ እድገት ውስንነት የተጠቁ ልጆችን ከተደበቁት አዉጥቶ ፍቅርና እንክብካቤ እንዲያገኙ እንዲሁም የመማር እና የመታከም መብታቸዉ እንዲጠበቅ በማድረጉ ታላቅ ምስጋና ይገባዋል።
በዚህ ዙሪያ የምትሰሩ አካላትን በሙሉ አቅሞቻችንን ሁሉ አሰባስበን በቅንጅት እንድንሰራ በመጠየቅ፣ የማህበረሰብ ለውጥ ለማምጣት ለምትሰሩት አኩሪ ስራ ምስጋናዬን አቀርባለሁ። በጤና ተቋሞቻችን በአእምሮ እድገት ውስንነት ለተጠቁ ህጻናት ነፃ የህክምና አገልግሎት የምንሰጥ መሆኑንም እገልጻለሁ። በተጨማሪም በዚሁ ዘርፍ ለተሰማሩ ትምህርት ቤቶች ድጋፍ እንደምናደርግ እና ተማሪዎችም በተማሩበት የሙያ ዘርፍ የስራ እድል እንዲያገኙ ሁኔታዎችን የምናመቻች መሆኑን ማሳወቅ እወዳለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.