ባለስልጣኑ በካሳንቺስ አካባቢ የተሰራው አዲስ የ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ባለስልጣኑ በካሳንቺስ አካባቢ የተሰራው አዲስ የኮሪደር ልማት በግዴለሽነት ጉዳት ያደረሰው ድርጅት 510 ሺህ ብር መቅጣቱ ገለፀ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በካዛንቺስ የኮሪደር ልማት አዲስ በተሰራው   የመንገድ መሠረተ ልማት ሜልኮን ኮንስትራክሽን የተባለ ድርጅት ኃላፊነት በጎደለው ሁኔታ ጉዳት ያደረሰው ድርጅቱ  500 ሺህ ብር እና ሁለት ሹፌሮች እያንዳንዳቸው 5 ሺህ ብር በድምሩ 510,000 ብር መቅጣቱ ገለፀ።

ድርጅቱ በቸልተኝነት የተሰራው የእግረኞች መንገድ ኮንክሪት ስታምፕ በማውደሙ ለፈጸመው ግዴየለሽነት ተግባር የገንዘብ ቅጣት  በመቅጣት  አስተዳደራዊ እርምጃ ተወስዶበታል፡፡

ባለስልጣኑ ድርጅቱ ከገንዘብ ቅጣቱ በተጨማሪ ያወደመውን የእግረኞች መንገድ ከተቀጣበት ሰዓት ጀምሮ በራሱ ወጪ በመገንባት እንዲያስተካክል ውሳኔ የተሰጠው መሆኑንም አሳውቋል።

ህግ በማስከበሩ ሂደት የከተማ አስተዳደሩ  አዲስ አበባን እንደ ስሟ አበባ በማድረግ የአፍሪካ ብልጽግና ማዕከል ለማድረግ ቀንና ሌሊት በሚሰራበት በዚህ ሰዓት  እንደዚህ አይነት ተግባር መፈፀም አሳፊሪ መሆኑ ተገልጿል።

ባለስልጣኑ በከተማው በልማት ስራ የተሰማሩ ድርጅቶችና ግለሰቦች መሠል ድርጊቶች ከመፈጸም እንዲቆጠቡ እያሳሰበ ደንብ በሚተላለፉት ላይ ደንብ የማስከበሩ ስራ ተጠናክሮ  አንደሚቀጥል አስታውቋል።

መረጃው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.