
የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ገቢውች ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የክትትል ኦፊሰር ባለሞያ በቁጥጥር ስር ዋሉ።
በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በወረዳ 2 በሰላምና ፀጥታ ኃላፊ የሚመራው የክትትል ቡድን በማደራጀት ከአያት አደባባይ እስከ ጣፎ አደባባይ ድረስ መንግስትና ህዝብ የሠጣቸውን ኃላፊነት ወደ ጎን በመተው ለራስ ያልተገባ ጥቅም በማዋል መኪናዎችን በማስቆም ገንዘብ ሲቀበሉ የነበሩ የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ገቢዎች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሰራተኛ ላይ እርምጃ ተወሰደ።
ይህንን ወንጀል ሲፈፅሙ እጅ ከፈንጅ የተያዙት ተጠርጣሪ ወንጀለኞች ስማቸው ከዚህ በታች የተዘረዘሩት
1. ዳኛቸው ጎንፋ ዋቅጅራ ባለሙያ
2. ዳዊት ፍቅሬ
3. ይልቃል ጌጤ (ሹፌር) ሲሆኑ እጅ ከፍንጅ ቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን ግለሰቦቹ በፈፀሙት ያልተገባ ውንጀል ምርመራ እየተደረገባቸው ይገኛል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.