
የአዲስ አበባ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የልዩ ወረዳ አመራርና አባላት ከመጋቢት እስከ መጋቢት :-" ትናንት ፣ ዛሬ እና ነገ ለኢትዮጵያ ልዕልና ! " በሚል መሪቃል ዉይይት አከሔዱ::
ብልፅግና በ7 ዓመታት ጉዞ ዉስጥ የተለያዩ ፈተናዎችን በማለፍ አስተሳሳሪ ና የወል ትርክት ለዘላቂ አንድነት፣በሠላም ማስፈንና በዲሞክራሲ ግንባታ፣የሀገራችንን ከተሞች የማዘመን ትልምና የኮሪደር ልማት ስራዎች፣ከተረጂነት ወደ ምርታማነት አሻጋሪ ሠዉ ተኮር ስራዎች፣ኢትዮጽያ ታምርት፣የገቢ አቅም በማሳደግ፣የኢኮኖሚና የተቋማት ሪፎርም፣ዲፕሎማሲያዊ ስራዎችና ብሔራዊ ጥቅምን ማስጠበቅ፣አምራች ኢንዱስትሪ በማስፋፋት የኢትዮጽያ ምርታማነትን ማሳደግ፣የከተማችንን የቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ የተሰራ ስራ :የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ላይ እና የሀገራችንን ፀጋ ለሀገራችን ብልፅግና በመጠቀም ረገድ አስደማሚ ለዉጦችን ተጨባጭ እዉነታዎች መሆናቸዉ በዉይይቱ ተመላክቷል።
በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉትት በአዲስ አበባ የብልፅግና ፓርቲ የከንቲባ የልዩ ወረዳ ሰብሳቢ አቶ ሞላ ንጉስ እንደገለፁት እንደብልፅግና መጋቢት ወርን ስናነሳ አዲስ አበባ ከተማን ብቻ ማየት በቂ መሆኑን ጠቅሰው በዉጪ አካላት አግራሞት የተፈጠረበት በዉስጥ አመራራችንና አባላችን እንደሚቻል በተግባር ተምረን ታሪካዊ ለዉጦችን ማረጋገጥ የቻልንበት ነዉ ብለዋል።
ብልፅግና ሁሉ ነገሩ ለሠዉ የሚሠራ ሠዉን የሚጠቅም አስተሳሳሪ ስራዎችን በመሥራት እንደ ሃገር ለትዉልድ ዘላቂ መሠረቶችን የጣለ መሆኑን የተናገሩት አቶ ሞላ ንጉስ የሀሳብ የበላይነትን ይበልጥ በማጠናከር በሁሉም ዘርፎች አካታችነትን በማጎልበት ተጨማሪ ስኬቶች ማስመዝገብ ይጠበቅብናልም ሲሉ መልዕክታቸዉን አስተላልፈዋል።
እንደ ሃገር እነዚህን ለውጦች ለማስቀጠል የብሄራዊነት ገዢ ትርክት ግንባታን በማጠናከር ቅቡልነት ያለው ጠንካራ ሀገረ መንግሥት እውን ለማድረግ የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ እናትዓለም መለስ ተናግረዋል ፡፡
የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው በተለይም በአዲስ አበባ ከተማ የተገኙ ለውጦችን በሁሉም አካባቢዎች ማስፋትና ማስቀጠል እንደሚገባ ለዚህም መላዉ አባላችን በትጋትና በቁርጠኝነት መስራት እንደሚጠበቅበት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.