የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ጋር በስልክ ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም በአፍሪካ ቀንድ መረጋጋት እና ሁለቱ ሃገራት በጋራ ቅድሚያ በሚሰጣቸው ጉዳዮች ዙሪያ የሁለትዮሽ ግንኙነቱን ለማጠናከር ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን ከስቴት ዲፓርትመንት ድረ-ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ማርኮ ሩቢዮ የኢትዮጵያ መንግስት ሰላሟ የተጠበቀ እና የበለፀገች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ እየሰራ ላለው ስራ የአሜሪካ መንግስት ድጋፉን እንደሚያጠናክር ማረጋገጣቸውን ዘገባው አመላክቷል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.