ዛሬ ማለዳ የኢድ አልፈጥር በዓልን ምክንያት በማ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ዛሬ ማለዳ የኢድ አልፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ 100 ሺሕ ለሚሆኑ አቅመ ደካሞች እና በዝቅተኛ የገቢ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ነዋሪዎቻችን ማዕድ አጋርተናል።ከንቲባ አዳነች አቤቤ

የማዕድ ማጋራቱ በሁሉም ክፍለ ከተሞች፣ ወረዳዎች እና የከተማ አስተዳደሩ ተቋማት በመካሄድ ላይ የሚገኝ ሲሆን የዕዝነትና የመረዳዳት ወር በሆነው የረመዳን ጾም ወቅት ጠያቂ ያጡ አስታዋሽ አግኝተው በቸርነት ተጎብኝተዋል፣ ደጋፊ ያልነበራቸው በልበ ቀናዎች እጅ ተዳብሰዋል።

ሰርተው ካገኙት መስጠትና ማካፈልን ባህል በማድረግ እንደ ወትሮው ሁሉ ዘንድሮም ከጎናችን የቆሙትን የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ እና በሁሉም ክፍለከተሞች አስተዋፅዖ ያደረጉ አካላትን በነዋሪዎቻችን እና በከተማ አስተዳደራችን ስም ላመሰግናቸው እወዳለሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.