በመዲናዋ በሁሉም የሠንበት ገበያዎችና የገበያ ማ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በመዲናዋ በሁሉም የሠንበት ገበያዎችና የገበያ ማዕከላት በቂ የምርት አቅርቦት መኖሩንና የተረጋጋ የገበያ ስርአት እየተከናወነ መሆኑን ተገለፀ

ይህ የተገለፀዉ "መጭውን የረመዳን በዓልን ምክንያት በማድረግ በ11ዱም ክፍለ ከተሞችና በሁሉም ወረዳዎች በሚገኙ የሠንበት ገበያዎችና የገበያ ማዕከላት  ላይ በተደረገዉ የመስክ ክትትልና ቁጥጥር ምልከታ ነዉ።

በመዲናችን በ11ዱም ከፍለ ከተሞችና በሁሉም  ወረዳዎች በሚገኙ የሠንበት  ገበያዎችና የገበያ ማዕከላት "መጭውን የረመዳን በዓል ምክንያት በማድረግ የፍጆታና ሌሎች ምርት አቅርቦት እጥረት እንዳያጋጥም እና  የተረጋጋ የገበያ ስርዓት እንዲኖር በቅድመ ዝግጅት ወቅት  ከማዕከል እስከ ወረዳ የተቀናጀና የተደራጀ የህገወጥ ንግድ ቁጥጥር ግብረ ሀይል ስምሪት አሰጣጥና ቅንጅታዊ  ክትትልና ግምገማ  በመሠራቱ መሆኑ ተገልጿል።

በዚህም   በ11ዱም ክፍለከተሞችና በሁሉም ወረዳዎች  በሚገኙ የሠንበት ገበያዎችና የገበያ ማዕከላት  ላይ በተደረገዉ የመስክ ክትትልና ቁጥጥር ምልከታ በቂ የግብርና እና የኢንዱስትሪ እንዲሁም ሌሎቾ  የምርት አቅርቦት መኖሩ  የተረጋጋ የገበያ ስርአት እየተከናወነ መሆኑን እና የገበያ ማዕከላት ምቹ መደረጋቸዉንም   ክፍለ ከተሞች ጠቅሰዉ በዘላቂነትም በሁሉም የግብይት ቦታዎች የክትትል  ድጋፍ እና   ቁጥጥር ስራንዎችን በማጠናከር በቂ የምርት አቅርቦት እንዲኖር በማድረግና  ተመጣጣኝ የዋጋ ግብይትን በማስፈን የማህበረሰባችንን ፍትሀዊ ተጠቃሚነት ይበልጥ እናረጋግጣለን ብለዋል።

በተጨማሪም ተገንብተዉ ወደ ስራ የገቡ  ሱፐር ማርኬትና ፍሬሽ ኮርነር  የገበያ ማረጋጋት ስራውን አጠናክረው እንዲቀጥሉም ተጠቁሟል።

በሌላ በኩል በዓሉን በማስመልከት ያለ አግባብ ጭማሬ እንዲፈጠር የሚያደርጉ እንዲሁም  የንግድ ፍቃድ የሌላቸውንና የገበያ ቦታውን ለማወክ  በህገወጥነት በተሠማሩ አካላት ላይ   ህጋዊ እርምጃ ለመዉሠድ  ከፀጥታ መዋቅሩ ባሻገር  የነጋዴዎችና የደላላዎች አደረጃጀት ተፈጥሮ ወደ ስራ መግባቱን ጠቅሰዉ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት  እንደሚሰሩ  ለህብረተሰቡ መልዕክታቸዉን አስተላልፈዋል።

ሸማቹ ኅብረተሰብ በገበያ እንቅስቃሴው ላይ ህገወጥ ድርጊቶች ሲያጋጥሙት በአቅራቢያቸዉ ባሉ የህግ አካላትና ተቋማት እንዲሁም በሌሎች አማራጮች ጥቆማዎችን እንዲሠጥ ጥሪ አቅርበዋል።።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.