1446ኛው የኢድ አልፈጥር ረመዳን ክብረ በዓል...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

1446ኛው የኢድ አልፈጥር ረመዳን ክብረ በዓል ጋር ተያይዞ የኢድ ሶላት ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

ነገ መጋቢት 21 ቀን 2017 ዓ/ም የሚከበረውን 1446ኛውን የኢድ አልፈጥር ረመዳን በዓል ያለ ምንም የጸጥታ ችግር እንዲከበር የጸጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል ቅድመ ዝግጅቱን አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱ የሚታወስ ሲሆን በዓሉን ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ የሚከናወነው የኢድ ሶላት ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ፡፡ 

በመሆኑም የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር አሽከርካሪዎች ከዚህ በታች የተገለፁት መንገዶች ዝግ መሆናቸውን ተገንዝበው ሌሎች አማራጮችን እንዲጠቀሙም የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳስቧል፡፡ 

በዚህም መሰረት፡-
👉 ከመገናኛ በ22 አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ቅዱስ ዑራኤል  አደባባይ በተመሳሳይ ከቦሌ አካባቢ በአትላስ መብራት ወደ ቅዱስ ዑራኤል አደባባይ ለሚሄዱ አትላስ መብራት እና ፒኮኪ መብራት ላይ፣
👉 ከቦሌ ወሎ ሠፈር መታጠፊያ ወደ ኦሎምፒያ አደባባይ ለሚሔዱ አሽከርካሪዎች ኦሎምፒያ አደባባይ ላይ፣ 
👉 ከወሎ ሠፈር ጀምሮ እስከ ጋዜቦ አደባባይ ውስጥ ውስጡን ወደ ዋናው መንገድ የሚያስወጡት መንገዶች ዝግ የሚደረጉ ይሆናል፣
👉 ከአጎና መስቀለኛ ወደ ጥላሁን አደባባይ -ሳንጆሴፍ መብራት አጎና ሲኒማ መስቀለኛ ላይ፣
👉 ከቡልጋሪያ መብራት ወደ ገነት ሆቴል ሜክሲኮ አደባባይ  ለሚሄዱ አሽከርካሪዎች ቡልጋሪያ መብራት ላይ፣
👉 ከቅድስት ልደታ ፀበል በAU ቅዱስ ሚካኤል መታጠፊያ ወደ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ AU ሚካኤል መታጠፊያ፣ 
👉 ከጦር ኃይሎች በከፍተኛ ፍ/ቤት  ወደ ሜክሲኮ አደባባይ ለሚሔዱ ከፍተኛ ፍ/ቤት አደባባይ ላይ፣ 
👉 ከአብነት አካባቢ በፈረሰኛ ፖሊስ  መብራት ወደ ጨፌ ሜዳ መብራት  ፈረሰኛ መብራት ላይ፣
👉 ከሞላ ማሩ መስቀለኛ ወደ ጌጃ ሰፈር መውረጃ ሞላ ማሩ መታጠፊያ ላይ፣ 
👉 ከመርካቶ አካባቢ በአቡነ ተክለ ኃይማኖት አደባባይ ወደ ጥቁር አንበሳ ለሚሄዱ አቡነ ተክለ ኃይማኖት አደባባይ ላይ ዝግ ይደረጋል።
👉 ከፒያሳ በባንኮዲሮማ መብራት ወደ ቴዎድሮስ አደባባይ ባንኮዲሮማ መብራት ላይ፣ 
👉 ከሲግናል አካባቢ በሴቶች አደባባይ ወደ ካዛንቺስ ለሚሄዱ ተሽከርካሪዎች ሴቶች አደባባይ ላይ ከንጋቱ 11:00 ሰዓት ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ድረስ መንገዶቹ ዝግ ይሆናሉ። 

ከዚህ በተጨማሪም ዛሬ ከበዓሉ ዋዜማ ምሽት ጀምሮ በተጠቀሱት ቦታዎች ላይ ተሽከርካሪዎችን ለአጭርም ይሁን ለረጅም ሠዓት ማቆም የተከለከለ ሲሆን ህብረተሰቡም ከፖሊስ የሚሰጠውን መረጃ ተገንዝቦ የትራፊክ ፖሊስ አባላት በሚጠቁሙት አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀም እና ለትራፊክ ፖሊስ አባላት ትዕዛዝ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪውን እያስተላለፈ ለእምነቱ ተከታዮች በሙሉ በዓሉ የፍቅርና የሠላም እንዲሆን  መልካም ምኞቱን ይገልፃል፡፡
ኢድ ሙባረክ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.