
አቶ አባስ መኮንን ድጋፍ ላደረጉላቸው ለክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ምስጋና አቅርበዋል::
የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር 1446 ኛው የኢድ አል-ፈጥር በዓልን አስመልክቶ በክፍለ ከተማው አቅም ለሌለውና ሁለቱንም እጆች በአደጋ ምክንያት ላጣ የወረዳ 07 አካል ጉዳተኛ ነዋሪ በዛሬው እለት የክብርት ከንቲባ የረመዳን የበአል የቤት ስጦታን አስተላልፏል።
ክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ በተገኙበት በከተማ አስተዳደሩ አቅም ለሌላቸው እና አነስተኛ ገቢ ላላቸው ነዋሪዎች በተዘጋጀው የኢፍጣር ፕሮግራም ላይ የተገኙትና ሁለቱንም እጆቹን በአደጋ ምክንያት አካል ጉዳተኛ ለሆነው የ3 ልጆች አባት ነዋሪነቱ በክፍለ ከተማው ወረዳ 07 ለሆነው አቶ አባስ መኮንን በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ኒዕመተላህ ከበደ አማካኝነት የረመዳን በአልን በማስመልከት በዛሬው እለት የቤት ስጦታ ተበረከተለት።
የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ኒዕመተላህ ከበደ በዚህ ወቅት በከተማችን የሰው ተኮር ተግባራትን በመፈፀም አነስተኛ ገቢ እና አቅመ የሌላቸው ዜጎችን የኑሮ ሁኔታ እንዲሻሻል ዘርፈ ብዙ ስራ መሰራቱን አንስተው የዛሬው የቤት ስጦታ የዚህ አካል ነው ብለዋል፤ የክፍለ ከተማው አስተዳደር ቋሚ የስራ እድል እንደሚፈጥርለትም ተናግረዋል።
ድጋፍ የተደረገላቸው አቶ አባስ መኮንን በበኩላቸው ድጋፍ እንዲደረግ ላደረጉት ለከተማዋ ከንቲባ ክብርት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እንዲሁም ድጋፉን በማመቻቸት ላስረከበው ለክ/ከተማው አስተዳደር ምስጋና አቅርበዋል።
ሰው ተኮር ተግባሮቻችን ለአብሮነታችን
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.