ዛሬ በከተማችን ያለውን የቡዝሃን ትራንስፖርት እ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ዛሬ በከተማችን ያለውን የቡዝሃን ትራንስፖርት እጥረት እና የነዋሪዎችን እንግልት የሚቀንሱ 100 ዘመናዊ የኤሌክትሪክ አውቶቡሶችን በመግዛት ወደ ስምሪት አስገብተናል።

የITS (ኢንተለጀንት የትራንስፖርት ሥርዓት) እና FCS (የታሪፍ ስብስብ ሥርዓት) ቴክኖሎጂን በተቀናጀ መልኩ በስራ ላይ ያዋሉት እነዚህ አውቶቢሶች ከአየር ብክለት ነፃ፣ ምቹ፣ በአንድ ጊዜ በርካታ የሠው ቁጥር ማጓጓዝ የሚችሉ፣ ዘመናዊና ተደራሽ፣ ወጪ ቆጣቢ፣ አስተማማኝ፣ ለአውቶቡስ ብቻ በተፈቀደ መስመር ስለሚጓዙ ፈጣን አገልግሎት የሚሰጡ እንዲሁም ለነዳጅ ይወጣ የነበረውን ወጪ የሚቀንሱ ናቸው።

ወደ አገልግሎት የገቡት እነዚህ 100 የኤሌክትሪክ አውቶቡሶች በዛሬው እለት በሁሉም የከተማችን አቅጣጫዎች ለነዋሪዎቻችን ነጻ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ይሆናል።

የህዝባችንን እንግልት ለመቀነስ የጀመርነውን ራዕይ በመጋራት በመንግስትና የግል አጋርነት መርሃግብር የመጀመሪያው የትራንስፖርት ኦፕሬተር በመሆን ዛሬ አገልግሎት መስጠት የጀመረውን የበላይነህ ክንዴ ግሩፕ በነዋሪዎቻችን ስም ላመሰግነው እወዳለሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
   ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
  https://linktr.ee/   addisababacommunication


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.