
በየአካባቢው የተገነቡና የህዝባችንን የኑሮ ደረጃ እያሻሻሉ ፣ የከተማችንንም የሀገራችንንም ገፅታ እየቀየሩ የሚገኙት ግዙፍ ልማቶች ከጠዋት እስከ ማታ ፣ ከመጋቢት እስከ መጋቢት በተደረገው ቅንጅታዊ ርብርብ የተመዘገቡ የለውጡ ፍሬዎች ናቸው።
በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች ፣ የሀይማኖት አባቶች ፣ የሀገር ሽማግሌዎች ፣ ሴቶች ፣ ወጣቶች ፣ የፀጥታ አካላት እና ሌሎችም የህብረተሰብ ክፍሎች ከመጋቢት እስከ መጋቢት ባለፉት የለውጥ ዓመታት በከተማችን የተገነቡ ግዙፍና ሰው ተኮር የልማት ፕሮጀክቶችን እየጎበኙ ሲሆን ለላቀ ድል ተጨማሪ ተነሳሽነትን እንደሚሰንቁም ይጠበቃል።
" ትናንት ፣ ዛሬ እና ነገ ለኢትዮጵያ ልዕልና ! "
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.