"የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

"የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት አገልግሎትን በማቀላጠፍ አርዓያነት ያለው ተግባር እየሰራ ነው!" - ዶ/ር አለሙ ስሜ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማችን ያለውን የትራንስፖርት ችግር የሚያቃልሉ 100 ዘመናዊ የኤሌክትሪክ አውቶቡሶችን በመንግስት እና ግል አጋርነት ወደ አገልግሎት ባስገባበት መርሃ ግብር ላይ የተገኙት የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክ ሚኒስትር ዶ/ር አለሙ ስሜ መልዕክት አስተላልፈዋል::

በመልዕክታቸውም በፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ውስጥ ያለችው ሀገራችን ኢትዮጵያን የኢኮኖሚ እድገትና የብልጽግና ጉዞ ለማስቀጠል የትራንስፖርት ዘርፉ አስቻይ የሆነ ወሳኝ ሚና መጫወት አለበት ያሉት ዶ/ር አለሙ ስሜ አዲስ አበባ የትራንስፖርት አገልግሎትን በማቀላጠፍ ረገድ አርዓያነት ያለው ተግባር እየሰራች ነው ብለዋል::

በትራንስፖርት ምክንያት በመንገድ ላይ የሚጠፋ ጊዜ ማጠር አለበት ያሉት ሚኒስትሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በዘርፉ ያለውን ችግር በዘላቂነት ለመቅረፍ በርካታ ስራዎችን እየሰራ የሚገኝ ሲሆን በዚህም መንገዶች እየሰፉ፣ የእግረኛ እና የተሽከርካሪ መንገዶች እየተለዩ፣ አዳዲስ መንገዶችም እየተገነቡ እንዲሁም ለህብረተሰቡ የትራንስፖርት አማራጮች እየቀረቡለት ይገኛሉ ብለዋል::

የትራንስፖርት እንቅስቃሴን የሚያደናቅፉ አላስፈላጊ ኬላዎችም በአዲስ አበባ የሉም ይህ ሁሉ ሲታይ አዲስ አበባ የትራንስፖርት አገልግሎትን በማቀላጠፍ አርዓያነት ያለው ተግባር እየሰራ ነው ያሉት ዶ/ር አለሙ ስሜ ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ ተስማሚ የሆኑና ያለንን ታዳሽ ሀይል የሚጠቀሙ ተሽከርካሪዎችን ወደ ስራ ለማስገባት በወጣው ፖሊሲ መሠረት ዛሬ ወደ ስራ የገቡት አውቶቢሶች ይህንን ለመፈጸም አይነተኛ ማሳያ ናቸው ብለዋል።

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች

https://linktr.ee/ addisababacommunication


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.