
ኃላፊነትና ተጠያቂነትን በማረጋገጥ የመንግስት ሀበትና ንብረት ከብክነት እና ምዝበራ እንከላከል በሚል መርህ ሀሳብ የውይይት መድረክ ተካሄደ።
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት በመንግስት በጀት አስተዳደርንና ቁጥጥር ጉዳዬች ቋሚ ኮሚቴ ክትትልና ቁጥጥር ከሚደረግላቸው ተቋማት አንዱ የሆነው ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት፣ በአዲስ አበበባ ከተማ ም/ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪን ጨምሮ ባለድርሻ አካላትና የተመረጡ ኦዲት ተደራጊ ተቋማት በተገኙበት ውይይት ተካሄደ።
በከተማችን ውስጥ ያሉ የመንግስት ተቋማት ሀብት ህግና ስርዓት ተከትለው እንዲተዳደሩና ለታለመላቸው ዓላማ እንዲውሉ ትልቅ ኃላፊነት የተሰጣችሁ አስፈፃሚ አካላት እንደመሆናችሁ መጠን የተሰጣችሁን ኃላፊት እና ተልዕኮ በአግባቡ መወጣት አለባችሁ ሲሉ የአዲስ አበባ ዋና ኦዲት መስሪያ ቤት ኃላፊ አቶ አመንቴ መቻሉ በመክፈቻ ንግግራቸው ጠቁመዋል ።
አክለውም ተቋማት ለረጅም ዓመት ሲንከባለሉ የነበሩ የኦዲት ግኝቶችን የማስተካከያ ስራ በመስራትና የእርምት እርምጃ እየወሰዱ መምጣታቸውን በማስታወስ ፤ በዛሬው ዕለትም አጠቃላይ ስለ ኦዲት አደራረግና የህግ ተጠያቂነት ስርዓት ከማስፈን አንፃርና የማስተካከያ እርምጃ አወሳሰድ ላይ ያተኮረ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤትም የኦዲት ፎረም በማጠናከር፣ ፎረሙን በህግ እና አሰራር ማደራጀት፣የክትትል እና ግምገማ አሰራር እና ሥርዓት በግልጽ ማስቀመጥ፣ የከተማው እና የክፍለ ከተማውን የኦዲት ፎረም አፈጻጸም በጋራ ወይም በተናጥል መድረክ መገምገም እንዲሁም የህግ ተጠያቂነት እንዲተገበር ግፊት ማድረግ እንደሚገባ ተገለፀ ።
የኦዲት ግኝቶችን መቀነስ የሚቻለው የውስጥ ኦዲተሮችን በማጠናከር ነው የሚጀምረው ያሉት የመንግስት በጀት አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ስንታየሁ ደስታ በክትትልና ቁጥጥር ስራችን በርካታ የኦዲት ግኝቶች እናገኛለን በተለይ አሰራሩን ጠብቆ ግዥ ካለመፈፀም የሚስተዋሉ ችግሮችና እንዲሁም የቆዩቱን ግኝቶት በመመሪያው መሠረት ከማስመለስ ጋር በተያያዘ አቅጣጫ እንሰጣለን ነገር ግን የእርምት እርምጃ ከመውሰድ አንፃር ውስንነቶች አሉና መታየት አለበት ሲሉ ጠቁመዋል ።
ተቋሙ ከአደረጃጀት እና ሪፎርም ጀምሮ ራሱን እያሻሻለ መምጣቱንና የዚህ ውጤት መነሻ እንደሆነ የተናገሩት በአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ የተከበሩ አቶ ማሾ ኦላና ከቀረበው ሪፖርት አንፃር የኛ ተቋም ምን ደረጃ ላይ ነን ብለን በመፈተሽ ቀጣይ ቀሪ ወራት ህጉንና ስርዓቱን ያማከለ ስራ በመስራት የጋራ መግባባት በመፍጠር የተጀመሩትን የልማት ስራዎች ከግብ ማድረስ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/ addisababacommunication
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.