
አዲስ አበባ በማያቋርጥ የለውጥ ጎዳና ላይ ናት !!
ዛሬ ወደ አገልግሎት ያስገባናቸው እነዚህ 100 ዘመናዊ የኤሌክትሪክ አውቶቢሶች ጠዋትና ማታ በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ ያለውን የትራንስፖርት ሰልፍ እና የህዝብ እንግልት የሚቀንሱ በሌላ በኩል ደግሞ መንግስት ያወጣውን የአየር ብክለት የመከላከል ፖሊሲን በተሟላ ሁኔታ መተግበር ብሎም በከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ የሚገባውን ነዳጅ እና የሚደርሰውን ጫና ለመቀነስ የሚረዱ ናቸው::
እነዚህ የኤሌክትሪክ አውቶቢሶች ዲጂታል ትኬቲንግ ስርዓትን ተግባራዊ የሚያደርጉ፣ ዲጅታል ባስ ካርድ ሥርዓት(Bus Card System) እውን የሚያደርጉ፣ በካሜራ እና ጂፒኤስ ድጋፍ እና ቁጥጥር የሚደረግባቸው እንዲሁም ሃገር ውስጥ የበለፀገ ሲስተም ተገጥሞላቸኋል።
የትራንስፖርት አገልግሎትን ለማሳለጥ እና ጥራትና ፈጣን የሆነ አገልግሎት ለህዝብ ለመስጠት ከለውጥ በፊት የነበረዉን የአውቶቢስ ቁጥር በእጥፍ ጨምረናል፣ ከለውጡ በፊት ከ 20% በታች የነበረውን የመንገድ ሽፋን በ10% ከፍ ማድረግ ችለናል ።
ተርሚናሎችን እና የመኪና ማቆሚያዎችን በአስር እጥፍ ማሳደግ የቻልንበት መሰረታዊ ለዉጥ መጋቢት 24 የተጀመረው ለውጥ ያመጣው መሰረታዊ ዉጤት ነው::
ዛሬ የግል ኦፕሬተርን ወደ ስራ ማስገባታችን በአሰራራችን እና በአገልግሎታችን ላይ አዳዲስ አሰራሮችን ወደ ስራ በማስገባት የበለጠ ህዝባችንን በቅንነትና በታማኝነት ለማገልገል ያለንን ቁርጠኝነታችንን ያሳየንበት ነው::
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/ addisababacommunication
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.