"አብሮ መስራትና ማደግ የተረጋገጠበት፤ለትዉልድ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

"አብሮ መስራትና ማደግ የተረጋገጠበት፤ለትዉልድ ዘላቂ መሠረት የጣሉ ፍትሀዊ የልማት ስራዎችን ማየት በመቻላችን ኩራት ተሠምቶናል!" ጎብኚዎች

በመዲናችን የሚገኙ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን በዛሬው እለት በከተማችን የተሰሩና እየተሰሩ ያሉ የልማት ስራዎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

ዓድዋ መታሰቢያን መነሻ አድርጎ በከተማዋ የተሠሩ የኮሪደር ልማቶች፤የወንዞች ተፋሰስና የወንዝ  ዳርቻ የልማት ስራዎች፤ፕላዛዎች፤የመንገድ ግንባታና የመሠረተ ልማት ዝርጋታዎች፤የአዲስ ዓለም ዓቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል፤የለሚ ኩራ የግብርና ምርቶች የገበያ ማዕከል አና የገላን ጉራ የተቀናጀ የጋራ መኖሪያ መንደር ተጎብኝተዋል።

ጎብኚዎቹ እንደተናገሩት በአጭር ጊዜ ጥራታቸዉን የጠበቁ ለአፍሪካ ኩራትና ተመራጭ የሆኑ፤የልማት ስራዎችን መሰራት መቻላችን  ለቀጣይ ትዉልድ በሚደረገዉ የጋራ ሀገር ግንባታ ሒደት ላይ ሁላችንም የበኩላችንን ለመወጣት ተነሳሽነትና ቁርጠኝነትን ፈጥሮብናል በማለት ገልፀዋል፡፡

በኢኮኖሚ፤በማህበራዊ እና በፖለታካ ዘርፈ ብዙ ስኬቶች የተመዘገቡበት የልማት ስራዎቻችንን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ጎብኚዎች ጠቅሰዉ ለተሠራዉም ስራ እዉቅና መስጠትና የራስን ታሪክ ማጉላት  ከዚህ ትዉልድ የሚጠበቅ ነዉ ሲሉ ጎብኚዎቹ ገልፀዋል።

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
  https://linktr.ee/   addisababacommunication


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.